am_tn/ezk/15/01.md

3.4 KiB

የእግዚአብሔር ቃል መጣ

ይህ እግዚአብሔር ለነቢያቱ ወይም ለሕዝቡ አንድን ነገር ለማስታወቅ የሚጠቀምበት የአነጋገር ዘይቤ ነው። ይህንን በሕዝቅኤል 3፡16 ላይ እንዴት እንደተረጎምከው ተመልከት። አ.ት፡ “እግዚአብሔር ይህንን መልዕክት ተናገረ” ወይም “እነዚህን ቃላት እግዚአብሔር ተናገረ” (የአነጋገር ዘይቤ የሚለውን ተመልከት)

የሰው ልጅ

“የሰብዓዊ ፍጡር ልጅ” ወይም “ከሰው የተወለደ ልጅ”። ሕዝቅኤል ሰው ብቻ መሆኑን አፅንኦት ለመስጠት እግዚአብሔር ሕዝቅኤልን እንዲህ በማለት ይጠራዋል። እግዚአብሔር ዘላለማዊና ኃያል ነው፣ ሰዎች ግን አይደሉም። አ.ት፡ “ሟች ሰው” ወይም “ሰው”

በደን ውስጥ በዛፎች መካከል ከሚገኙ ቅርንጫፎች ካሏቸው ዛፎች ሁሉ የወይን ሐረግን የተሻለ የሚያደርገው ምንድነው?

ሕዝቅኤል አስቀድሞ ስለሚያውቀው ስለ አንድ ነገር ለማስታወስ እግዚአብሔር ይህንን ምላሽ የማይሻ ጥያቄ ይጠይቀዋል። ይህ እንደ ንግግር ሊተረጎም ይችላል። አ.ት፡ “የወይን ሐረግ በደን ውስጥ ከሚገኝ ቅርንጫፍ ካለው ከየትኛውም ዛፍ የተሻለ አይደለም” (ምላሽ የማይሻ ጥያቄ የሚለውን ተመልከት)

ሰዎች የሆነ ነገር ለመሥራት ከወይን ሐረግ እንጨትን ይወስዳሉ?

ሕዝቅኤል አስቀድሞ ስለሚያውቀው ስለ አንድ ነገር ለማስታወስ እግዚአብሔር ይህንን ምላሽ የማይሻ ጥያቄ ይጠይቀዋል። ይህ እንደ ንግግር ሊተረጎም ይችላል። አ.ት፡ “ሰዎች የሆነ ነገር ለመሥራት ከወይን ሐረግ እንጨትን አይወስዱም” (ምላሽ የማይሻ ጥያቄ የሚለውን ተመልከት)

የትኛውንም ነገር ያንጠለጥሉበት ዘንድ ከእርሱ መስቀያ ያበጁበታል?

ሕዝቅኤል አስቀድሞ ስለሚያውቀው ስለ አንድ ነገር ለማስታወስ እግዚአብሔር ይህንን ምላሽ የማይሻ ጥያቄ ይጠይቀዋል። ይህ እንደ ንግግር ሊተረጎም ይችላል። አ.ት፡ “ነገሮችን በእርሱ ላይ ለመስቀል ከእርሱ መስቀያን አያበጁም” (ምላሽ የማይሻ ጥያቄ የሚለውን ተመልከት

እንዲነድ እሳት ላይ ቢጥሉት … ለአንዳች ነገር ይጠቅማል?

ሕዝቅኤል አስቀድሞ ስለሚያውቀው ስለ አንድ ነገር ለማስታወስ እግዚአብሔር ይህንን ምላሽ የማይሻ ጥያቄ ይጠይቀዋል። ይህ እንደ ንግግር ሊተረጎም ይችላል። አ.ት፡ “እንዲነድ እሳት ላይ ቢጥሉት … ለምንም አይጠቅምም” (ምላሽ የማይሻ ጥያቄ የሚለውን ተመልከት

እንዲነድ እሳት ላይ ቢጥሉት

ይህ በአድራጊ ድምፅ ሊነገር ይችላል። አ.ት፡ “አንድ ሰው እንዲነድ እሳት ላይ ቢጥለው” (አድራጊ ወይም ተደራጊ ድምፅ የሚለውን ተመልከት)