am_tn/ezk/13/20.md

1.8 KiB

ወፎችን ይመስል የሕዝቡን ሕይወት ለማጥመድ የምትጠቀሙበት የአስማት ክታብ

ሰዎቹ ሴቶች በክታቦቻቸው የሚያጠምዷቸውን ወፎች ይመስል እግዚአብሔር የአስማት ክታባቸውን በመጠቀም ሰዎችን ስለሚያሳስቱ ስለ እነዚህ ሴቶች ይናገራል። (ዘይቤአዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)

ክታብ

አስማታዊ ኃይል አላቸው ተብለው የሚታመኑ ቁሳቁሶች

ለማጥመድ

“ለመያዝ” “በወጥመድ ለመያዝ”

ከክንዳችሁ ላይ እቀድዳቸዋለሁ

“ክታቦቹን ከክንዶቻችሁ ላይ እቀድዳለሁ”

ሕዝቤን ከእጃችሁ አድናቸዋለሁ

እዚህ ጋ “እጅ” የሚለው ቃል የሚወክለው ኃይልን ወይም መቆጣጠርን ነው። አ.ት፡ “ሕዝቤን ከኃይላችሁ አድናቸዋለሁ” (ፈሊጣዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)

ከእንግዲህ በእጆቻችሁ አይጠመዱም

እዚህ ጋ “እጅ” የሚለው ቃል የሚወክለው ኃይልን ወይም መቆጣጠርን ነው። ሴቶቹ ሰዎቹን በእጆቻቸው ያጠመዷቸው ይመስል ሰዎቹ በእነዚህ ሴቶች ቁጥጥር ስር ስለ መሆናቸው እግዚአብሔር ይናገራል። ይህ በአድራጊ ድምፅ ሊነገር ይችላል። አ.ት፡ “በእጆቻችሁ እንዳለ የሚታደን እንስሳ ከእንግዲህ አታጠምዷቸውም” ወይም “ከእንግዲህ በኃይላችሁ አትቆጣጠሯቸውም” (ፈሊጣዊ አነጋገር፣ ዘይቤአዊ አነጋገር እና አድራጊ ወይም ተደራጊ ድምፅ የሚለውን ተመልከት)