am_tn/ezk/13/17.md

3.5 KiB

ፊትህን በሴቶቹ ልጆች ላይ አቅና

ይህ ሴቶቹን የመቅጣት ምልክት ይሆን ዘንድ እነርሱን አፍጥጦ እንዲመለከት የተሰጠ ትዕዛዝ ነው። “በእነርሱ ላይ ፊትህን አቅና” የሚለውን በሕዝቅኤል 4፡3 ላይ እንዳደረግኸው ተርጉም። አ.ት፡ “በሴቶቹ ልጆች ላይ አፍጥጥባቸው”

በእነርሱ ላይ ፊትህን አቅና

እዚህ ጋ “ፊት” በትኩረት ወይም በጥሞና የመመልከት ፈሊጣዊ አነጋገር ነው፣ “ፊትህን አቅና” የሚወክለው አፍጥጦ መመልከትን ነው። አ.ት፡ “አፍጥጠህ እይ” (ፈሊጣዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)

የሕዝብህ ሴቶች ልጆች

የአነጋገር ዘይቤው እንደ ሕዝቅኤል ሁሉ የዚያው ሕዝብ ወገን የሆኑትን ሴቶች ያመለክታል። አ.ት፡ “የእስራኤል ሴቶች” ወይም “የሀገርህ ሴቶች” (የአነጋገር ዘይቤ የሚለውን ተመልከት)

ከራሳቸው አዕምሮ አውጥተው ይተነብያሉ

“በገዛ ራሳቸው አዕምሮ ያሰቧቸውን ነገሮች ብቻ እየተነበዩ” ተመሳሳዩን ሐረግ በሕዝቅኤል 13፡2 ላይ እንዴት እንደ ተረጎምከው ተመልከት።

በ -- ላይ ትንቢት ተናገር

“ስለሚደርሱባቸው አስከፊ ነገሮች ትንቢት ተናገር”። ይህንን በሕዝቅኤል 4፡7 ላይ እንዴት እንደ ተረጎምከው ተመልከት።

በእጆቻቸው ሁሉ ላይ የአስማት ክታብ ሰፍተዋል

ይህ ማለት የአስማቱን ክታቦች በአንድ ላይ በመስፋት በእጆቻቸው ላይ አስረውታል ማለት ነው እንጂ በቀጥታ በእጆቻቸው ላይ ሰፍተውታል ማለት አይደለም።

ክታብ

አስማታዊ ኃይል አለው ተብሎ የሚታመንበት ቁስ

ሰዎችን ለማጥመድ ተጠቅመውበታል

እግዚአብሔር ስለ እነዚህ ሴቶች በክታቦቻቸው አማካይነት እንስሶችን አድነው ያጠምዱ ይመስል ሰዎችን ለማሳሳት ውበታቸውን፣ ምስጢራቸውንና ውሸታቸውን እንደሚጠቀሙ እግዚአብሔር ይናገራል። ይህ በአድራጊ ድምፅ ሊነገር ይችላል። አ.ት፡ “ሰዎችን ለማጥመድ የሚጠቀሙባቸው” (ዘይቤአዊ አነጋገር እና አድራጊ ወይም ተደራጊ ድምፅ የሚለውን ተመልከት)

ለራሳቸው የተለያየ መጠን ያለው መሸፈኛ ያበጃሉ

ይህ ማለት የተለያየ ቁመት ባላቸው ሰዎች ራስ ላይ ለማድረግ መሸፈኛዎችን ያበጃሉ። አ.ት፡ “የተለያየ ቁመት ላላቸው ሴቶች ራስ መሸፈኛዎችን ያበጃሉ”

ሕዝቤን አጥምዳችሁ የገዛ ራሳችሁን ሕይወት ታድናላችሁ?

እነዚህን ነገሮች የሚያደርጉትን ሴቶች ለመገሰጽ እግዚአብሔር ይህንን እንደ ዋነኛ ጥያቄ አድርጎ ይጠይቃል። ይፋ ያልሆነው መልስ “አይደለም” የሚል ነው። አ.ት፡ “ሕዝቤን ካጠመዳችሁ በኋላ የገዛ ራሳችሁን ሕይወት ማዳን እንደምትችሉ አታስቡ!” (ምላሽ የማይሻ ጥያቄ የሚለውን ተመልከት)