am_tn/ezk/13/13.md

1.6 KiB

ዐውሎ ንፋስ አመጣለሁ … ፈጽሞ ያጠፋዋል።

እግዚአብሔር ግንቡን የሚያፈራርስ ብርቱ ዐውሎ በሚመስል መልኩ በሕዝቡ ላይ የሚልከውን ፍርድ ያመለክታል። (ዘይቤአዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)

በመዓቴ … በቁጣዬ … በመዓቴ

“በመዓቴ ምክንያት … በቁጣዬ ምክንያት … በመዓቴ ምክንያት”

ተገልጦ ይቀራል

“አይሸፈንም”

በመካከሏም ድምጥማጣችሁ ይጠፋል

“በመካከሏ” የሚለው ቃል እግዚአብሔር የሚያፈርሰውን የግንቡን ድንጋዮች ያመለክታል። ግንቡ በሚፈርስበት ጊዜ ይገድላቸው ይመስል እግዚአብሔር ሕዝቡን በፍርዱ እንደሚያጠፋቸው ይናገራል።(ዘይቤአዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)

ድምጥማጣቸው ይጠፋል

“ይጠፋሉ”

እኔ እግዚአብሔር እንደ ሆንኩ ያውቃሉ

እግዚአብሔር ሰዎች እርሱ እግዚአብሔር መሆኑን ያውቃሉ ብሎ በሚናገርበት ጊዜ እርሱ ፍጹም ኃይልና ሥልጣን ያለው ብቸኛው እውነተኛ አምላክ መሆኑን ሰዎች ያውቃሉ ማለቱ ነው። ይህንን በሕዝቅኤል 6፡7 ላይ እንዴት እንደ ተረጎምከው ተመልከት። አ.ት፡ “እውነተኛው አምላክ እኔ እግዚአብሔር መሆኔን ይረዳሉ” ወይም “ፍጹም ኃይልና ሥልጣን ያለኝ እኔ እግዚአብሔር መሆኔን ይገነዘባሉ”