am_tn/ezk/13/10.md

2.6 KiB

በዚህ ምክንያት

“በዚህ” የሚለው ቃል ሐሰተኛ ራዕዮችን ለሕዝቡ የሚያስታውቁትንና ውሸትን የሚነግሯቸውን ነቢያት ያመለክታል።

ሕዝቤን አስተዋል

ነቢያቱ ሕዝቡ ይሄዱበት ከነበረው መንገድ ላይ ያሳቷቸው ይመስል ሕዝቡን ስለማሳሳታቸውና ውሸትን እንዲያምኑ ስለማድረጋቸው እግዚአብሔር ይናገራል። (ዘይቤአዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)

በኖራ የሚለስኑትን ግንብ ይገነባሉ

እዚህ ጋ፣ “ግንብ” የቆመው እግዚአብሔር ለሕዝቡ ሊሰጣቸው ቃል ለገባውና ሐሰተኞቹ ነቢያት ለሕዝቡ ለነገሯቸው ለሰላምና ደህንነት ነው። (ዘይቤአዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)

ኖራ … በኖራ መለሰን

“ኖራ” የሚለው ቃል የሚያመለክተው የተበላሸውን ለመሸፈንና ገጽታውን ነጭ ለማድረግ ጥቅም ላይ የሚውለውን የነጭ ፈሳሽ ውሁድ ወይም ቀለምን ነው።

እርሱን እንዲጥለው የበረዶ ድንጋይን፣ ሰባብሮ እንዲጥለውም ዐውሎ ነፋስን እልካለሁ

እግዚአብሔር ግንቡን እንደሚያፈራርስ ብርቱ ዐውሎ በሚመስል መልኩ በሕዝቡ ላይ የሚልከውን ፍርዱን ያመለክታል። (ዘይቤአዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)

የበረዶ ድንጋይ

በዶፍ ዝናብ ወቅት አንዳንዴ ከሰማይ የሚወድቁ ሁሉም ዓይነት በረዶዎች

ሌሎች፣ “የለሰናችሁበት ኖራ የት አለ?” አላሏችሁም?

ሌሎች ኖራዎቻቸው ምን እንደሆነባቸው ነቢያቱን እንደሚጠይቋቸው አጽንዖት ለመስጠት እግዚአብሔር ይህንን ምላሽ የማይሻ ጥያቄ ይጠይቃል። አ.ት፡ “ያለ ጥርጥር ሌሎች እንዲህ ይሏችኋል፣ ‘የለሰናችሁበት ኖራ የት አለ’ “(ምላሽ የማይሻ ጥያቄ የሚለውን ተመልከት)

የለሰናችሁበት ኖራ የት አለ?

ሊሆኑ የሚችሉ ትርጉሞች 1) ይህ ሕዝቡ የሚገምተውና የሚመልሰው ቅንነት ያለበት ጥያቄ ነው ወይም 2) ይህ ሕዝቡ በፌዝ የሚጠይቀው ምላሽ የማይሻ ጥያቄ ነው የሚሉት ናቸው። አ.ት፡ “የለሰናችሁበት ኖራ ምንም አልጠቀመም”። (ምላሽ የማይሻ ጥያቄ የሚለውን ተመልከት)