am_tn/ezk/13/08.md

2.9 KiB

ይህ የጌታ እግዚአብሔር ንግግር ነው

እግዚአብሔር የንግግሩን እርግጠኝነት ለመግለጽ የራሱን ስም በመጥራት ይናገራል። ይህንን በሕዝቅኤል 5፡11 ላይ እንዴት እንደተረጎምከው ተመልከት።አ.ት፡ “ጌታ እግዚአብሔር የተናገረው ይህንን ነው” ወይም “እኔ፣ ጌታ እግዚአብሔር የተናገርኩት ይህንን ነው” (አንደኛ፣ ሁለተኛ ወይም ሦስተኛ መደብ የሚለውን ተመልከት)

እጄ በነቢያት ላይ ትሆናለች

እዚህ ጋ፣ “እጅ” የሚለው ቃል የሚወክለው የእግዚአብሔርን ኃይል ነው። እጁ በእነርሱ ላይ መሆኗ ዘይቤአዊ አነጋገር ሲሆን ትርጉሙም እርሱ በኃይሉ ይቀጣቸዋል ማለት ነው። አ.ት፡ “ነቢያትን እቀጣቸዋለሁ” (ፈሊጣዊ አነጋገር እና ዘይቤአዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)

በሕዝቤ ጉባዔ ውስጥ አይሆኑም

ይህ ማለት እግዚአብሔር እነዚህን ሐሰተኞች ነቢያት የእስራኤል ሕዝብ አካል አድርጎ አይቆጥራቸውም።

ወይም በእስራኤል ቤት መዝገብ አይጻፉም

ይህ ምናልባት የእስራኤል ዜጎች የሚመዘገቡበትን መንግሥታዊ መዝገብ ያመለክት ይሆናል። ይህ በአድርጊ ድምፅ ሊነገር ይችላል። አ.ት፡ “በእስራኤል ቤት መዝገብ ላይ ማንም ስማቸውን አይጽፍም” (አድራጊ ወይም ተደራጊ ድምፅ የሚለውን ተመልከት)

የእስራኤል ቤት

“ቤት” የሚለው ቃል በቤቱ ውስጥ የሚኖሩትን ቤተሰቦች የሚያመለክት ፈሊጣዊ አነጋገር ነው፤ በመሆኑም፣ ይህ ከረጅም ዓመታት ጀምሮ ያሉትን የያዕቆብን ዘሮች፣ እስራኤላውያንን ያመለክታል። ይህንን በሕዝቅኤል 3፡1 ላይ እንዴት እንደተረጎምከው ተመልከት። አ.ት፡ “የእስራኤል ሕዝብ ወገን” (ፈሊጣዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)

እኔ ጌታ እግዚአብሔር መሆኔን ታውቃላችሁ

እግዚአብሔር ሰዎች እርሱ እግዚአብሔር መሆኑን እንደሚያውቁ በሚናገርበት ጊዜ እርሱ ፍጹም ኃይልና ሥልጣን ያለው ብቸኛው እውነተኛ አምላክ መሆኑን ያውቃሉ ማለቱ ነው። ይህንን በሕዝቅኤል 6፡7 ላይ እንዴት እንደ ተረጎምከው ተመልከት። አ.ት፡ “እውነተኛው አምላክ እኔ እግዚአብሔር መሆኔን ትረዳላችሁ” ወይም “ፍጹም ኃይልና ሥልጣን ያለኝ እኔ ጌታ እግዚአብሔር መሆኔን ትገነዘባላችሁ”