am_tn/ezk/13/05.md

1.8 KiB

በእስራኤል ቤት ዙሪያ ያለውን ግንብ

ይህ የኢየሩሳሌምን ከተማ የሚከብበውን ግንብ ያመለክታል።

የእስራኤል ቤት

“ቤት” የሚለው ቃል በቤቱ ውስጥ የሚኖሩትን ቤተሰቦች የሚያመለክት ፈሊጣዊ አነጋገር ነው፤ በመሆኑም፣ ይህ ከረጅም ዓመታት ጀምሮ ያሉትን የያዕቆብን ዘሮች፣ እስራኤላውያንን ያመለክታል። ይህንን በሕዝቅኤል 3፡1 ላይ እንዴት እንደተረጎምከው ተመልከት። አ.ት፡ “የእስራኤል ሕዝብ ወገን” (ፈሊጣዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)

በጦርነት መቋቋም

እዚህ ጋ ግልጽ ያልተደረገውን መረጃ መጨመር ትችላለህ። አ.ት፡ “የጠላትን ሰራዊት መቋቋም” ወይም “ከተማይቱን መከላከል”

የእግዚአብሔር ቀን

ይህ እግዚአብሔር በጠላት ሰራዊት አማካይነት በሕዝቡ ላይ የሚፈርድበትን ጊዜ ያመለክታል። አ.ት፡ “የእግዚአብሔር የፍርድ ቀን” ወይም “እንዲወጓችሁ እግዚአብሔር የጠላትን ሰራዊት በመላክ በእናንተ ላይ የሚፈርድበት ቀን”

እኔ ራሴ ባልተናገርኩበት ጊዜ ሐሰተኛ ራዕዮች አልነበሯችሁም?

ሐሰተኞቹን ነቢያት ለመገሰጽ እግዚአብሔር በጥያቄ መልክ ይናገራል። አ.ት፡ “እኔ ራሴ ያልተናገርኩት . . . ሐሰተኛ ራዕዮች ነበሯችሁ” (ምላሽ የማይሻ ጥያቄ የሚለውን ተመልከት)

ሐሰተኛ ራዕዮች ነበሯችሁ፣ የውሸት ትንቢትም ተናገራችሁ

x