am_tn/ezk/11/19.md

4.0 KiB

አንድ ልብ እሰጣቸዋለሁ … የሥጋ ልብ እሰጣቸዋለሁ

እግዚአብሔር አንድ ልብና አንድ መንፈስ እንዳለው እንደ አንድ ሰው አድርጎ የሚናገረው በምርኮ ስላሉት እስራኤላውያን ሁሉ ነው። (ዘይቤአዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)

አንድ ልብ እሰጣቸዋለሁ

እዚህ ጋ “ልብ” የሚለው ፈሊጣዊው አነጋገር የሚወክለው ፈቃድን እና ስሜትን ነው። እግዚአብሔር ለሕዝቡ ሁሉ አንድ ልብ የሰጣቸው ያህል ተመሳሳይ የሆነ አዲስ ስሜት እንደሚጋሩ ይናገራል (ፈሊጣዊ አነጋገር እና ዘይቤአዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)

አዲስን መንፈስ በውስጣቸው አደርጋለሁ

እዚህ ጋ “መንፈስ” የሚለው ፈሊጣዊ አነጋገር አሳብንና ጸባይን ይወክላል። እግዚአብሔር ለሕዝቡ አዲስ መንፈስ የሰጣቸው ያህል አዳዲስ አሳቦችን እንዲያስቡ እንደሚያደርጋቸው ይናገራል። (ፈሊጣዊ አነጋገር እና ዘይቤአዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)

ከሥጋቸው ውስጥ የድንጋይን ልብ አወጣለሁ፣ የሥጋንም ልብ እሰጣቸዋለሁ

ሕዝቡ የድንጋይ ልብ ስለነበራቸው እልኸኛ እንደሆኑና የሥጋ ልብ ሲኖራቸው በፈቃደኝነት የሚታዘዙ እንደሚሆኑ እግዚአብሔር ይናገራል። ሁለቱን ልቦች በማቀያየር በፈቃደኝነት የሚታዘዙ እንደሚያደርጋቸው ይናገራል። አ.ት፡ “እልኸኛ መሆናቸውን እንዲያቆሙ አደርጋቸዋለሁ፣ በምትኩም በፈቃደንነት እንዲታዘዙኝ አደርጋቸዋለሁ” (ዘይቤአዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)

በትዕዛዛቴ ይሄዳሉ፣ ሕግጋቴንም ይፈጽማሉ፣ ያደርጓቸዋልም

እነዚህ ሐረጎች ሁሉ ሕዝቡ እግዚአብሔር እንዲያደርጉት ያዘዛቸውን እንደሚታዘዙ የሚገልጽ ተመሳሳይ ትርጉም አላቸው። የተደጋገሙት አጽንዖት ለመስጠት ነው። (See: Parallelism)

በትዕዛዛቴ ይሄዳሉ

እግዚአብሔር የእርሱን ትዕዛዛት መጠበቅ አንድ ሰው በመንገድ ላይ እንደሚሄድ ሁሉ በትዕዛዛቱ ላይ እንደ ሄደ አድርጎ ይናገራል። አ.ት፡ “ትዕዛዛቴን ይጠብቃሉ” (ዘይቤአዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)

ወደ አስከፊ ነገሮቻቸው በውዴታ የሚሄዱትን እነዚያን

እግዚአብሔር ስለ አንድ ሰው ሥራ ሲናገር ያ ሰው ተራምዶ እንደሚሄድ አድርጎ ይናገራል። አ.ት፡ “ሕይወታቸውን አስከፊ የሆኑ ነገሮቻቸውን ለመሥራት በትጋት የሚሰጡትን እነዚያን” (ዘይቤአዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)

የሚያስከፉ ነገሮች

ይህ የሚያስጠሉና የሚያስቀይሙ ነገሮችን ማለት ነው። እዚህ ጋ፣ ይህ የሚያመለክተው ጣዖታትን ነው። ይህንን በሕዝቅኤል 11፡18 ላይ እንዴት እንደተረጎምከው ተመልከት።

ሥራቸውን በራሳቸው ላይ አመጣባቸዋለሁ

እዚህ ጋ “ሥራ” የሚለው ፈሊጣዊው አነጋገር የሚወክለው የድርጊቶቻቸውን ውጤት ነው። “በራሳቸው ላይ አመጣባቸዋለሁ” የሚለው የአነጋገር ዘይቤ ትርጉሙ ውጤቱን ይቀበላሉ የሚል ነው። አ.ት፡ “በድርጊቶቻቸው ምክንያት በውጤቱ መከራን እንዲቀበሉ አደርጋቸዋለሁ” (ፈሊጣዊ አነጋገር እና የአነጋገር ዘይቤ የሚለውን ተመልከት)