am_tn/ezk/11/16.md

1.6 KiB

መቅደሳቸው ሆኜ ነበር

እግዚአብሔር በምርኮ ባለው ሕዝብ መካከል ማደሩን ሲገልጽ መቅደስ እንደሆነላቸው አድርጎ ይናገራል። አ.ት፡ “ከእነርሱ ጋር ነበርኩ” ወይም “እንደ አምልኮ ስፍራቸው ነበርኩ” (ዘይቤአዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)

ከሕዝቦች መካከል እሰበስባችኋለሁ፣ ከየሀገራቱም መልሼ አከማቻችኋለሁ

በመሠረቱ የእነዚህ ሁለት ሐረጎች ትርጉም አንድ ነው። ድግግሞሹ አጽንዖት የሚሰጠው እግዚአብሔር ምርኮኞቹን ወደ እስራኤል ምድር ለመመለስ የሰጠው ተስፋ እርግጥ መሆኑን ነው። አ.ት፡ “ከየሀገራቱ ሁሉ መልሼ አመጣችኋለሁ”

ከተበተናችሁበት

ይህ በአድራጊ ድምፅ ሊነገር ይችላል። አ.ት፡ “እናንተን ከበተንኩበት” (አድራጊ ወይም ተደራጊ ድምፅ የሚለውን ተመልከት)

የሚያስከፋውን ነገር ሁሉ እና የሚያስጸይፈውን ተግባር ሁሉ

እነዚህ ሁለት ሐረጎች ተመሳሳይ ትርጉም ያላቸው ሲሆኑ እግዚአብሔር ጣዖታትን ሁሉ ከእስራኤል እንደሚያስወግድ አጽንዖት ይሰጣሉ።

የሚያስከፋውን ነገር ሁሉ

ይህ ማለት የሚያስጠሉ ወይም የሚያስቀይሙ ነገሮችን ማለት ነው። እዚህ ጋ፣ ይህ የሚያመለክተው ጣዖታትን ነው።