am_tn/ezk/11/14.md

2.0 KiB

የእግዚአብሔር ቃል መጣ

ይህ እግዚአብሔር ለነቢያቱ ወይም ለሕዝቡ አንድን ነገር ለማስታወቅ የሚጠቀምበት የአነጋገር ዘይቤ ነው። ይህንን በሕዝቅኤል 3፡16 ላይ እንዴት እንደተረጎምከው ተመልከት። አ.ት፡ “እግዚአብሔር ይህንን መልዕክት ተናገረ” ወይም “እነዚህን ቃላት እግዚአብሔር ተናገረ” (የአነጋገር ዘይቤ የሚለውን ተመልከት)

ወንድሞችህ! ወንድሞችህ!

ይህ አጽንዖት ለመስጠት ሁለት ጊዜ ተነግሯል

የእስራኤል ቤት

“ቤት” የሚለው ቃል በቤቱ ውስጥ የሚኖሩትን ቤተሰቦች የሚያመለክት ፈሊጣዊ አነጋገር ነው፤ በመሆኑም፣ ይህ የያዕቆብን ዘሮች፣ እስራኤላውያንን ያመለክታል። ይህንን በሕዝቅኤል 3፡1 ላይ እንዴት እንደተረጎምከው ተመልከት። አ.ት፡ “የእስራኤል ሕዝብ” (ፈሊጣዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)

እነዚያ ሁሉ በኢየሩሳሌም በሚኖሩት የተነገረላቸው ናቸው

ይህ በአድራጊ ድምፅ ሊነገር ይችላል። አ.ት፡ “በኢየሩሳሌም የሚኖሩ ሰዎች ስለ እነርሱ ስለ ሁሉም ይናገራሉ” (አድራጊ ወይም ተደራጊ ድምፅ የሚለውን ተመልከት)

እነዚያ ሁሉ የተነገረላቸው ናቸው

አንዳንድ ትርጉሞች “ሁሉም የእነርሱ ናቸው” የሚል አላቸው

ይህቺ ምድር ርስታችን ሆና ተሰጥታናለች

ይህ በአድራጊ ድምፅ ሊነገር ይችላል። አ.ት፡ “እግዚአብሔር ይህቺን ምድር ርስት አድርጎ ሰጥቶናል” ወይም “ይህቺ ምድር ርስታችን ሆናለች” (አድራጊ ወይም ተደራጊ ድምፅ የሚለውን ተመልከት)