am_tn/ezk/11/11.md

1.2 KiB

ይህቺ ከተማ የማብሰያ ማሰሮ አትሆንላችሁም፣ እናንተም ሥጋ አትሆኑም

ሕዝቡ ስለ ራሳቸው የተከተፈ ሥጋ እንደሆኑና ከተማይቱም እንደ ሥጋ ማስቀመጫ ወይም ማብሰያ ማሰሮ እንደሆነች አድርገው ተናግረው ነበር። እግዚአብሔር ይህ እውነት አይደለም ይላል። ይህንን ዘይቤአዊው አነጋገር በሕዝቅኤል 11፡3 ላይ እንዴት እንደተረጎምከው ተመልከት። አ.ት፡ “ማሰሮ ሥጋን እንደሚከልል ይህቺም ከተማ እንደ ማሰሮ አትከልላችሁም” (ዘይቤአዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)

በእስራኤል ድንበር ውስጥ

“በእስራኤል ምድር”

በትዕዛዛቱ አልሄዳችሁም

ሰው በመንገድ ላይ እንደሚሄድ ትዕዛዛቱን የሚጠብቁ በእነርሱ ላይ እንደሚሄዱ አድርጎ እግዚአብሔር ይናገራል። አ.ት፡ “ትዕዛዛቱን ያልጠበቃችሁለት እርሱ” (ዘይቤአዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)