am_tn/ezk/11/02.md

1.8 KiB

የሰው ልጅ

“የሰብዓዊ ፍጡር ልጅ” ወይም “ከሰው የተወለደ ልጅ”። ሕዝቅኤል ሰው ብቻ መሆኑን አፅንዖት ለመስጠት እግዚአብሔር ሕዝቅኤልን እንዲህ በማለት ይጠራዋል። እግዚአብሔር ዘላለማዊና ኃያል ነው፣ ሰዎች ግን አይደሉም። ይህንን በሕዝቅኤል 2፡1 ላይ እንዴት እንደተረጎምከው ተመልከት። አ.ት፡ “ሟች ሰው” ወይም “ሰው”

ቤቶች የሚሠሩበት ጊዜ አሁን አይደለም

ይህ ሕዝቡ ደህንነት ስለተሰማቸው አሁን ላይ ቤት ለመሥራት እንዳላሳሰባቸው ያሳያል። ሌሎች የመጽሐፍ ቅዱስ ትርጉሞች “ቤቶቻችንን የምንሠራበት ጊዜ አሁን ነው” የሚል ይነበብባቸዋል። ይህም ማለት፣ ሕዝቡ ደህንነት ስለተሰማቸው ቤቶችን ለመሥራት ፈልገዋል።

ይህቺ ከተማ ማሰሮ ናት፣ እኛም ሥጋ ነን

ሕዝቡ ስለ ራሳቸው የተከተፈ ሥጋ እንደሆኑና ከተማይቱም እንደ ሥጋ ማስቀመጫ ወይም ማብሰያ ማሰሮ እንደሆነች አድርገው ይናገራሉ። ዘይቤአዊው አነጋገር በከተማይቱ ውስጥ እነርሱ አስፈላጊዎችና ጉዳት የማይደርስባቸው መሆናቸውን ይጠቁማል። አ.ት፡ “ማሰሮ ሥጋን እንደሚከልል ይህቺም ከተማ እንደ ማሰሮ ትከልለናለች” (ዘይቤአዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)

ማሰሮው

ሊሆኑ የሚችሉ ትርጉሞች 1) ሥጋ ለማስቀመጥ የሚያገለግል ማሰሮ ወይም 2) ሥጋ ለማብሰል የሚያገለግል ማሰሮ የሚሉት ናቸው።