am_tn/ezk/08/17.md

2.8 KiB

አንተ ሰው … ይህንን ታያለህ?

ሕዝቅኤል እያየ ስላለው ነገር እንዲያስብ እግዚአብሔር ያዘዋል። አ.ት፡ “ አንተ ሰው … ስለዚህ ነገር አስብ” (ምላሽ የማይሻ ጥያቄ የሚለውን ተመልከት)

በዚህ ቦታ እነዚህን አስጸያፊ ነገሮች ማድረጋቸው ለይሁዳ ቤት ይህ ቀላል ነገር ነው?

እግዚአብሔር በይሁዳ ቤት ላይ መቆጣቱ ትክክል መሆኑን ለማሳየት ይህንን ጥያቄ ያቀርባል። አ.ት፡ “በዚህ ቦታ በሚያደርጓቸው በእነዚህ አስጸያፊ ተግባሮች ምክንያት በይሁዳ ቤት ላይ ብቆጣ ልክ ነኝ” (ምላሽ የማይሻ ጥያቄ የሚለውን ተመልከት)

የይሁዳ ቤት

“ቤት” የሚለው ቃል በቤቱ ውስጥ የሚኖሩትን ቤተሰቦች የሚያመለክት ፈሊጣዊ አነጋገር ነው፤ በመሆኑም፣ ይህ ከረጅም ዓመታት ጀምሮ ያሉትን የይሁዳን ዘሮች ያመለክታል። እነዚን ቃላት በሕዝቅኤል 3፡1 ላይ እንዴት እንደ ተረጎምካቸው ተመልከት። አ.ት፡ “የይሁዳ ሕዝብ ወገን” ወይም “የይሁዳ ሕዝብ” (ፈሊጣዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)

ምድሪቱን በአመፅ ሞልተዋታል

“በሀገሩ ሁሉ የአመፅን ተግባር ይፈጽማሉ” ወይም “በሀገሪቱ ሁሉ እርስ በእርሳቸው ይገዳደላሉ”

ቁጣዬን ለማነሣሣት

“እንድቆጣ ለማድረግ”

ቅርንጫፉን ወደ አፍንጫዎቻቸው አቅርበዋል

ሊሆኑ የሚችሉ ትርጉሞች 1) ሰዎቹ ለሐሰተኛ አምልኮ ቅርንጫፎችን ይጠቀሙ ነበር ወይም 2) ሰዎቹ በእግዚአብሔር ላይ ማመፃቸውን ለማሳየት ቅርንጫፎቹን ይጠቀሙባቸው ነበር የሚሉት ናቸው። “ቅርንጫፍ… ወደ አፍንጫዎቻቸው” የሚሉት ቃላት ምናልባት በቀጥታ የዛፍ ቅርንጫፍና አፍንጫን ያመለክት ይሆናል ወይም የእጅ እንቅስቃሴን የሚገልጽ ስያሜ ይሆናል። (የአነጋገር ዘይቤ የሚለውን ተመልከት)

ዓይኔ ርኅራኄ አይኖረውም

ዓይን ባለቤቱ የሆነውን ሰውን ይወክላል። አ.ት፡ “በርኅራኄ አልመለከታቸውም” ወይም “አልራራላቸውም”

አልምራቸውም

“ገና እቀጣቸዋለሁ”

በታላቅ ድምፅ በጆሮዬ ላይ ቢጮኹም እንኳን

“በታላቅ ድምፅ በጸሎታቸው ወደ እኔ ቢጮኹም”

አልሰማቸውም

“አላዳምጣቸውም”