am_tn/ezk/08/12.md

1.1 KiB

የእስራኤል ቤት ሽማግሌዎች በጨለማው ውስጥ የሚያደርጉትን ታያለህ?

ሽማግሌዎቹ የሚያደርጉትን እንዲያይ እግዚአብሔር ሕዝቅኤልን እያዘዘው ነው። አ.ት፡ “የእስራኤል ቤት ሽማግሌዎች በጨለማው ውስጥ የሚያደርጉትን እይ”። (ምላሽ የማይሻ ጥያቄ የሚለውን ተመልከት)

የእስራኤል ቤት

“ቤት” የሚለው ቃል በቤቱ ውስጥ የሚኖሩትን ቤተሰቦች የሚያመለክት ፈሊጣዊ አነጋገር ነው፤ በመሆኑም፣ ይህ ከረጅም ዓመታት ጀምሮ ያሉትን የያዕቆብን ዘሮች፣ እስራኤላውያንን ያመለክታል። ይህንን በሕዝቅኤል 3፡1 ላይ እንዴት እንደ ተረጎምከው ተመልከት። አ.ት፡ “እስራኤላውያንን” ወይም “የእስራኤል ሕዝብ ወገን” (ፈሊጣዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)

በጣዖቱ ድብቅ ጓዳ

“ጣዖቱን ሲያመልክ ማንም ሊያየው የማይችልበት ክፍል”