am_tn/ezk/08/10.md

1.8 KiB

እነሆ

ይህ ቃል የሚያሳየው ሕዝቅኤል ባየው ነገር መደነቁን ነው። የአንተ ቋንቋ ይህንን ለማሳየት ሌላ ቃል ይኖረው ይሆናል።

የተለያዩ በደረታቸው የሚሳቡ ነገሮች እና እርኩሳን አራዊት

“በግድግዳው ላይ የተቀረጹ፣ የተለያዩ በደረታቸው የሚሳቡ እንስሶች እና እርኩሳን አራዊት”። “በደረታቸው የሚሳቡ ነገሮች” የሚለው ሐረግ የሚያመለክተው ነፍሳትን እና ሌሎች ትናንሽ እንስሶችን ነው።

የእስራኤል ቤት

“ቤት” የሚለው ቃል በቤቱ ውስጥ የሚኖሩትን ቤተሰቦች የሚያመለክት ፈሊጣዊ አነጋገር ነው፤ በመሆኑም፣ ይህ ከረጅም ዓመታት ጀምሮ ያሉትን የያዕቆብን ዘሮች፣ እስራኤላውያንን ያመለክታል። ይህንን በሕዝቅኤል 3፡1 ላይ እንዴት እንደ ተረጎምከው ተመልከት። አ.ት፡ “እስራኤላውያንን” ወይም “የእስራኤል ሕዝብ ወገን” (ፈሊጣዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)

ዙሪያውን በግንቡ ላይ

የትኛው ግንብ እንደሆነ ግልጽ ማድረግ ያስፈልግህ ይሆናል። አ.ት፡ “በቤተ መቅደሱ ዙሪያ ባለው ግንብ ላይ”

ያዕዛንያ … ሳፋን

የወንዶች ስም ነው (ስሞች እንዴት እንደሚተረጎሙ የሚለውን ተመልከት)

የዕጣን ማጨሻ

ሰዎች እግዚአብሔርን ወይም ሐሰተኞች አማልክትን በሚያመልኩበት ጊዜ ዕጣን የሚያጨሱበት ጎድጎድ ያለ ዕቃ