am_tn/ezk/08/05.md

2.1 KiB

የሰው ልጅ

“የሰብዓዊ ፍጡር ልጅ” ወይም “ከሰው የተወለደ ልጅ”። ሕዝቅኤል ሰው ብቻ መሆኑን አፅንኦት ለመስጠት እግዚአብሔር ሕዝቅኤልን እንዲህ በማለት ይጠራዋል። እግዚአብሔር ዘላለማዊና ኃያል ነው፣ ሰዎች ግን አይደሉም። ይህንን በሕዝቅኤል 2፡1 ላይ እንዴት እንደ ተረጎምከው ተመልከት። አ.ት፡ “ሟች ሰው” ወይም “ሰው”

ዓይኖችህን አንሣ … ዓይኖቼን አነሣሁ

ይህ የአነጋገር ዘይቤ የሚያሳየው ወደ አንድ ነገር መመልከት እንደነበረበት ነው። አ.ት፡ “ወደ ላይ እይ … ወደ ላይ አየ” ወይም “ፊትህን አዙርና ተመልከት … ፊቴን አዙሬ ተመለከትኩ” (የአነጋገር ዘይቤ የሚለውን ተመልከት)

ወደ መሰዊያው ወደሚያመራው በር

“ሰዎች ወደ መሰዊያው ለመድረስ አልፈው የሚሄዱበት በር”

የሚያደርጉትን ታያለህ?

የሕዝቅኤልን ትኩረት ሰዎቹ ወደሚያደርጉት ነገር ለማምጣት እግዚአብሔር ይህንን ጥያቄ ይጠቀማል። አ.ት፡ “ሰዎቹ እዚህ ጋ የሚያደርጉትን ነገር የምጠላበትን ምክንያት እንድትረዳ እፈልጋለሁ” (ምላሽ የማይፈልግ ጥያቄ የሚለውን ተመልከት)

የእስራኤል ቤት

“ቤት” የሚለው ቃል በቤቱ ውስጥ የሚኖሩትን ቤተሰቦች የሚያመለክት ፈሊጣዊ አነጋገር ነው፤ በመሆኑም፣ ይህ ከረጅም ዓመታት ጀምሮ ያሉትን የያዕቆብን ዘሮች፣ እስራኤላውያንን ያመለክታል። ይህንን በሕዝቅኤል 3፡1 ላይ እንዴት እንደ ተረጎምከው ተመልከት። አ.ት፡ “እስራኤላውያንን” ወይም “የእስራኤል ሕዝብ ወገን” (ፈሊጣዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)