am_tn/ezk/08/03.md

1.5 KiB

ያዘ

“እርሱ” የሚለው ቃል የሚያመለክተው ምናልባት “ሰው የሚመስለውን ምስል” ይሆናል (ሕዝቅኤል 8፡2)።

በሰማይና በምድር መካከል

“በመሬትና በጠፈር መካከል”

ከእግዚአብሔር በሆነው ራዕይ ወደ ኢየሩሳሌም አመጣኝ

“በራዕይ” የሚለው ቃል ትርጉም፣ ይህ ልምምድ የመጣው በሕዝቅኤል አሳብ ውስጥ ነው ማለት ነው። እግዚአብሔር እነዚህን ነገሮች በሚያሳየው ጊዜ አካሉ በዚያው በመኖሪያ ቤቱ ውስጥ ይሆናል ማለት ነው።

ሰሜናዊ ውስጠኛው በር

“የቤተ መቅደሱ ሰሜናዊ ውስጠኛው በር”። ቤተ መቅደሱ ውስጠኛና ውጪኛ በሆኑ ሁለት ግምቦች የተከበበ ነበር። ይህ በር በስተሰሜን በውስጠኛው ግምብ ላይ ነበረ።

ታላቅ ቅንዓት የሚያነሣሣው ጣዖት

“እግዚአብሔር በጣም እንዲቀና የሚያደርገው ጣዖት”

ሜዳው ላይ ዐይቼው እንደነበረው ራዕይ

ሊሆኑ የሚችሉ ትርጉሞች 1) “ሜዳው ላይ በነበርኩበት ጊዜ በራዕይ ዐይቼው የነበረውን ያንኑ የሚመስል” ወይም 2) “ሜዳው ላይ በነበርኩበት ጊዜ ያየሁትን ያንኑ የሚመስለውን” የሚሉት ናቸው።

ሜዳው

ጥቂት ዛፎች ያሉበት ዝርግ የሆነ ሰፊ መሬት