am_tn/ezk/08/01.md

2.6 KiB

እንዲህ ሆነ

እዚህ ጋ፣ ይህ ሐረግ ጥቅም ላይ የዋለው የታሪኩን አዲስ ክፍል ጅማሬ ለማመልከት ነው። የአንተ ቋንቋ ይህንን የሚያደርግበት መንገድ ካለ እዚህ ጋ ልትጠቀምበት እንደምትችል አስብ።

በስድስተኛው ዓመት

ይህ ስድስተኛ ዓመት የትኛውን ጊዜ እንደሚያመለክት ግልጽ ማድረግ ያስፈልግህ ይሆናል። አ.ት፡ “ንጉሡ ኢዮአቄም በተማረክ በስድስተኛ ዓመት”

በስድስተኛው ወር፣ በወሩም በአምስተኛው ቀን

ይህ በዕብራውያኑ የቀን አቆጣጠር ስድስተኛ ወር ነው። በምዕራባውያኑ አቆጣጠር አምስተኛው ቀን የመስከረም ወር መጀመሪያ አቅራቢያ ነው። አ.ት፡ “የስድስተኛው ወር አምስተኛ ቀን” (የዕብራውያን ወራት እና ደረጃን አመልካች ቁጥር የሚለውን ተመልከት)

የጌታ እግዚአብሔር እጅ እንደገና በእኔ ላይ ወደቀች

ኋላ ላይ ሕዝቅኤል እጅ የሚመስል ነገር ስለሚያይ ይህ በቀጥታ መተርጎም ይኖርበታል። ሌሎች እጁን የእግዚአብሔርን ኃልዎት ወይም ኃይል የሚያመለክት ዘይቤአዊ አነጋገር አድርገው ይመርጡት ይሆናል። (ዘይቤአዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)

ጌታ እግዚአብሔር

ይህንን በሕዝቅኤል 2:4 ላይ እንዴት እንደ ተረጎምከው ተመልከት።

በእኔ ላይ ወደቀች

“ያዘችኝ”

አንድ የሰው መልክ አምሳያ

እዚህ ጋ፣ የነገር ስም የሆነው “መልክ” ማለት ለሕዝቅኤል ሰው መስሎ የታየው ነገር ነው። “መልክ” እና “አምሳያ” ሁለቱም ከግሳዊ ሐረግ ጋር ሊተረጎሙ ይችላሉ። አ.ት፡ “አንድ ሰው የሚመስል ታይቶ ነበር” (የነገር ስም የሚለውን ተመልከት)

የጋለ ብረት

ብረት በጣም ሲሞቅ ይግልና ቢጫ ወይም ብርቱካናማ ቀለም ይኖረዋል።

የወገቡ አምሳያ … የሚያንጸባርቅ ነገር አምሳያ

የነገር ስም የሆነው “አምሳያ” እንደ ግሥ ሊተረጎም ይችላል። አ.ት፡ “ወገቡን መስሎ የታየው … አንጸባራቂ ነገር መስሎ የታየው” (የነገር ስም የሚለውን ተመልከት)