am_tn/ezk/07/26.md

1.6 KiB

ጥፋት በጥፋት ላይ ይመጣል

ጥፋት በራሱ ሊንቀሳቀስ እንደሚችል ተደርጎ ተነግሯል። አ.ት፡ “ከአንዱ ኋላ ሌላኛው ጥፋት ይመጣል” (ሰውኛ የሚለውን ተመልከት)

ከነቢይ ራዕይን ይፈልጋሉ

“ነቢያት ምን ዓይነት ራዕይ እንዳዩ ይጠይቋቸዋል”

ሕጉ ከካሕናት፣ ምክርም ከሽማግሌዎች ይጠፋል

“ካሕናቱ ሕጉን አያስተምሩም፣ ሽማግሌዎቹም ጥሩ ምክር ለመስጠት አይችሉም”። ይህ የሚሆነው እግዚአብሔር ጥበብን ስለማይሰጣቸው ነው።

መስፍኑ

ሊሆኑ የሚችሉ ትርጉሞች 1) “የንጉሡ ወንድ ልጅ” ወይም 2) ከንጉሡ ውጪ የንጉሣዊ ቤተሰብ አባላት የሆኑ ወንዶች ሁሉ የሚሉት ናቸው።

ተስፋ መቁረጥን ይለብሳሉ

ሊሆኑ የሚችሉ ትርጉሞች 1) ልብስ አንድ ሰው “ተስፋ አይኖራቸውም” ለሚል ስሜቱ ፈሊጣዊ አነጋገር ነው ወይም 2) “በማልቀስ ላይ መሆኑን የሚያሳይ ልብስ ይለብሳል” የሚሉት ናቸው። (የአነጋገር ዘይቤ እና ፈሊጣዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)

የምድሪቱ ሰዎች እጆቻቸው በፍርሐት ይንቀጠቀጣል

“እጆች” የሚለው ቃል ሕዝቡን ይወክላል። አ.ት፡ “የምድሪቱ ሕዝብ እጆቻቸው እስኪንቀጠቀጡ ድረስ እጅግ ይፈራሉ”