am_tn/ezk/07/23.md

2.5 KiB

ሠንሠለት አዘጋጅ

ሰንሰለት ባሮችን ወይም እስረኞችን ለማሰር ጥቅም ላይ ይውላል። እግዚአብሔር ይህንን የሚለው ሕዝቡ ባሮች ወይም እስረኞች እንደሚሆኑ ለማሳየት ነው።

ምድሪቱ በደም ፍርድ ተሞልታለች

ሊሆኑ የሚችሉ ትርጉሞች 1) “ሌሎችን በጭካኔ ገድለዋለና እግዚአብሔር በሀገሪቱ ሁሉ ላይ ይፈርዳል” ወይም 2) “በሀገሪቱ ውስጥ በየቦታው ያሉ ፍርድ ቤቶች ሰዎችን በመግደል ላይ ናቸው”። እዚህ ጋ፣ “ደም” የሚለው ቃል ግድያና ሞትን ይወክላል የሚሉት ናቸው። (ፈሊጣዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)

ከተማይቱ ጭካኔን ተሞልታለች

ከተማይቱ የዕቃ መያዣ በምትመስልበት መልኩ ተነግሮላታል፣ ጭካኔም በዕቃ መያዣ ውስጥ እንደሚደረግ ቁስ ተነግሮለታል። የነገር ስም የሆነው “ጭካኔ” እንደ ግሥ ሊተረጎም ይችላል። አ.ት፡ “በከተማይቱ ውስጥ ጭካኔ በየስፍራው አለ” ወይም “በከተማይቱ የሚኖሩ ብዙ ሰዎች በሌሎች ላይ የጭካኔ ተግባር እየፈጸሙባቸው ነው” (ዘይቤአዊ አነጋገር እና የነገር ስም የሚለውን ተመልከት))

እነርሱ ቤቶቻቸውን ይወርሳሉ

ክፉዎች የእስራኤላውያኑን ቤት ይወስዳሉ

ለኃያላኑ ትዕቢት መጨረሻን አደርጋለሁ

“በእስራኤል ውስጥ ያሉ ብርቱ ሰዎች በራሳቸው መመካታቸውን እንዲያቆሙ አደርጋለሁ”

ቅዱስ ስፍራዎቻቸው ሁሉ ይረክሳል!

ይህ በአድራጊ ድምፅ ሊተረጎም ይችላል። አ.ት፡ “የአምልኮ ስፍራዎቻቸውን ጠላት ያረክሳቸዋል” (አድራጊ ወይም ተደራጊ ድምፅ የሚለውን ተመልከት)

የተቀደሱ ስፍራዎቻቸው

ጣዖታትን የሚያመልኩባቸውን ስፍራዎች

ፍርሐት ይመጣል

“ሕዝቡ ይፈራል”

ሰላምን ይፈልጋሉ

“ከጠላቶቻቸው ጋር ሰላምን ለመፍጠር ይሞክራሉ”

ነገር ግን አንዱም አይሆንም

“ነገር ግን ከጠላቶቻቸው ጋር ሰላምን ለመፍጠር አይችሉም”