am_tn/ezk/07/17.md

2.3 KiB

እጅ ሁሉ ይዝላል፣ ጉልበትም ሁሉ እንደ ውሃ ይሆናል

እጆችና ጉልበቶች ስለ ሕዝቡ ስለ ራሱ የሚወክሉ ናቸው። አ.ት፡ “መሥራት እስከማይችሉ ድረስ ሁሉም እጅግ ይፈራሉ፣ ጉልበታቸውም መቆም እስከማይችል ድረስ ደካማ ይሆናል”

መዛል

መደረግ ያለበትን ለማድረግ አለመቻል

ጉልበት ሁሉ እንደ ውሃ ይሆናል

ሊሆን የሚችለው ሌላው ትርጉም፣ ሰዎቹ ሁሉ እጅግ ስለ ፈሩ ፊኛዎቻቸውን መቆጣጠር እንዳቃታቸው የሚያሳየው “ጉልበት ሁሉ ከውሃ ጋር ይንሳፈፋል” የሚለው ነው።

ጉልበት … እንደ ውሃ የደከመ

ውሃ ሊቆም አይችልም፣ ጉልበታቸው እጅግ ስለሚደክም ሕዝቡ በእግሮቻቸው ለመቆም አይችሉም። (See: Simile)

ሽብር ይሸፍናቸዋል

ሽብር እንደ ልብስ ተደርጎ ተነግሮለታል። አ.ት፡ “ምን ያህል እንደ ፈሩ ሁሉም ያያል” (ዘይቤአዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)

በራሳቸው ሁሉ ላይ በራነት

ጸጉርን መላጨት የሐዘን ምልክት ነበር። አ.ት፡ “ሁሉም ጸጉራቸውን ይላጫሉ”

በእግዚአብሔር የመዓት ቀን

“እግዚአብሔር በቁጣው በሚሠራበት ቀን” ወይም “እግዚአብሔር በሚቀጣቸው ጊዜ”

ቀኑ

ይህ 24 ሰዓት ካለው ቀን የበለጠ ወይም ያነሰ ጊዜ ሊሆን ይችላል።

ረሃባቸው አይረካም

ይህ በአድራጊ ድምፅ ሊተረጎም ይችላል። አ.ት፡ “ረሃባቸውን ለማርካት አይችሉም” ወይም “ያላቸውን ሁሉ ከበሉ በኋላ እንኳን ገና የተራቡ ይሆናሉ” (አድራጊ ወይም ተደራጊ ድምፅ የሚለውን ተመልከት)

ኃጢአታቸው ማሰናከያ ሆኖባቸዋል

ሊሆኑ የሚችሉ ትርጉሞች 1) “ምክንያቱም የነበራቸው ብዙ ወርቅና ብር ወደ ኃጢአት መርቷቸዋል” ወይም 2) “ክፉዎች ስለሆኑ፣ ምን ያህል ክፉዎች እንደሆኑ ለማሳየት ኃጢአትን ይሠራሉ” የሚሉት ናቸው።