am_tn/ezk/07/12.md

1.1 KiB

ጊዜው ደርሷል፤ ቀኑ ቀርቧል

“ጊዜው” እና “ቀኑ” ሁለቱም እግዚአብሔር የእስራኤልን ሕዝብ የሚቀጣበትን ጊዜ ያመለክታሉ። አ.ት፡ “የእስራኤል ቅጣት በቅርቡ ይደርሳል”

ቁጣዬ በመላው ሕዝብ ላይ ነው

“በመላው ሕዝብ ላይ ተቆጥቻለሁ”

በርካታ ሕዝብ

በጣም ብዙ ቁጥር ያለው ሕዝብ። እዚህ ጋ፣ ቃሉ የሚያመለክተው የእስራኤልን ሕዝብ ነው።

ሁለቱም በሕይወት እስካሉ ድረስ

“ገዢው” እና “ሻጩ” (7፡12) ሁለቱም በሕይወት እስካሉ ድረስ

መላውን ሕዝብ የሚመለከተው ራዕይ አይለወጥም

“እግዚአብሔር ያሳየኝን በመላው ሕዝብ ላይ በእርግጥ ያደርጋል”

አንዳቸውም አይበረቱም

ይህ በአድራጊ ድምፅ ሊተረጎም ይችላል። አ.ት፡ “እግዚአብሔር ማናቸውንም አያበረታም” (አድራጊ ወይም ተደራጊ ድምፅ የሚለውን ተመልከት)