am_tn/ezk/07/10.md

1.1 KiB

እነሆ ቀኑ! እነሆ ደርሷል!

“እነሆ! ቀኑ እየደረሰ ነው!” የትኛው ቀን እየደረሰ እንዳለ ግልጽ ማድረግ ያስፈልግህ ይሆናል። አ.ት፡ “እነሆ! አንቺን የምቀጣበት ቀን እየደረሰ ነው!”

እነሆ

“ተመልከት” ወይም “ስማ” ወይም “የምነግርህን ልብ በል”

የጥፋት ፍርድ ወጥቶ ሄዷል

“ጥፋት ወደ እስራኤል መምጣት ጀምሯል” ወይም “በጣም አስፈሪ ነገሮች መምጣት ጀምረዋል”

በትሩ አብቧል፣ እብሪት እምቡጥ ይዟል

ሊሆኑ የሚችሉ ትርጉሞች 1) “የእስራኤል ሕዝብ ትዕቢታቸውን አብዝተዋል” ወይም “የእስራኤል ሕዝብ በጣም ቁጡና ትዕቢተኛ ሆነዋል” (ዘይቤአዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)

ጭካኔ ወደ አመፅ በትርነት አድጓል

“የሕዝቡ አመፅ በይበልጥ ክፉ ነገሮችን ወደ ማድረግ መርቷቸዋል”