am_tn/ezk/07/08.md

1.3 KiB

ብዙም ሳይቆይ

“በጣም በቅርቡ”

በአንቺ ላይ ንዴቴን አፈሳለሁ፣ በላይሽ ላይ ቁጣዬን እሞላለሁ

እግዚአብሔር በእንስራ ውስጥ እንደሚያፈሰው ውሃ “አፈሳለሁ” እና “እሞላለሁ” የሚሉትን ቃላት የሚጠቀመው ስለ ቁጣው ለመናገር ነው። እነዚህ ሐረጎች እግዚአብሔር ሕዝቡን በአስከፊ ሁኔታ እንደሚቀጣቸው አጽንዖት ይሰጣሉ። አ.ት፡ “በጣም ስለተቆጣሁ በብርቱ እቀጣችኋለሁ” (ዘይቤአዊ አነጋገር እና Parallelism የሚለውን ተመልከት)

ንዴት

“ቁጣ” ወይም “ታላቅ ቁጣ”

ዐይኔ በርኅራኄ አይመለከትም

ዓይን ባለቤቱ የሆነውን ሰውን ይወክላል። አ.ት፡ “በርኅራኄ አልመለከታቸውም” ወይም “አልራራላቸውም”

አልምርሽም

“ያለ ቅጣት አልተውሽም” ወይም “እቀጣሻለሁ”

እኔ እግዚአብሔር መሆኔን ታውቂ ዘንድ አስጸያፊ ተግባርሽ በመካከልሽ ይሆናል

ይህንን በሕዝቅኤል 7:4 ላይ እንዴት እንደ ተረጎምከው ተመልከት