am_tn/ezk/07/05.md

1.6 KiB

ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል

እርሱ የሚናገረው አስፈላጊ መሆኑን ለሕዝቅኤልና ለሕዝቡ ለማስታወስ እግዚአብሔር ስለ ራሱ በስሙ ይናገራል። ይህንን በሕዝቅኤል 6፡11 ላይ እንዴት እንደ ተረጎምከው ተመልከት። አ.ት፡ “እኔ ጌታ እግዚአብሔር ይህንን እናገራለሁ” (አንደኛ፣ ሁለተኛ ወይም ሦስተኛ መደብ የሚለውን ተመልከት)

ጌታ እግዚአብሔር

ይህንን በሕዝቅኤልል 2:4 ላይ እንዴት እንደ ተረጎምከው ተመልከት።

ጥፋት! ለየት ያለ ጥፋት! እነሆ መጥቶአል

እነዚህ ቃለ-አጋኖዎች ምንባቡን በጣም ከባድ ያደርጉታል ማለት ነው። አ.ት፡ “እነሆ፣ ቀድሞ ማንም ያልተለማመደው ዓይነት አስከፊ ጥፋት እየመጣ ነው”

እነሆ፣ እርሱ

“እርሱ እንደሚሆን በፍጹም አትጠራጠሪ”

ፍጻሜ በአንቺ ላይ ተነሣሥቶአል

እየመጣ ያለው ፍርድ ከእንቅልፉ በሚነቃ ጠላት ተመስሎ ተነግሯል። (ሰውኛ የሚለውን ተመልከት)

ከእንግዲህ ተራሮች ደስተኞች አይሆኑም

“ተራሮች” የሚለው ቃል በተራሮች ላይ የሚኖሩትን ሰዎች የሚያመለክት ፈሊጣዊ አነጋገር ነው። አ.ት፡ “በተራሮች ላይ የሚኖሩት ሰዎች ከእንግዲህ ምንም ደስታ አይኖራቸውም” (ፈሊጣዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)