am_tn/ezk/07/03.md

2.2 KiB

ፍጻሜው በአንቺ ላይ ነው

ስለ “ፍጻሜ” የተነገረው ዘራፊ ሰዎችን እንደሚያጠቃቸው ተደርጎ ነው። አ.ት፡ “ሕይወትሽ አልቋል” (ሰውኛ የሚለውን ተመልከት)

ቁጣዬን እልክብሻለሁ

“ቁጣ” እግዚአብሔር በሰዎቹ ላይ እንደሚወረውረው ፍላጻ ሆኖ ተነግሯል። አ.ት፡ “ተቆጥቻለሁ፣ ስለዚህ እቀጣሻለሁ” (ዘይቤአዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)

እንደ መንገዶችሽ

“እንደምትሠሪያቸው ነገሮች” ወይም “በምትሠሪው ክፉ ነገሮች ምክንያት”

አስጸያፊነትሽን በሙሉ በአንቺ ላይ አመጣለሁ

“እነዚያን እጅግ የምጠላቸውን ነገሮች በማድረግሽ እቀጣሻለሁ”

ዓይኖቼ አይራሩልሽም

ዓይን ባለቤቱ የሆነውን ሰውን ይወክላል። አ.ት፡ “አልራራልሽም”

መንገድሽን በአንቺ ላይ አመጣለሁ

አንድ ሰው የሕይወት ዘይቤው እንደሚሄድበት ጎዳና ሆኖ ተነግሯል። አ.ት፡ “ስላደረግሻቸው ነገሮች እቀጣሻለሁ” (ዘይቤአዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)

አስጸያፊነትሽ በመካከልሽ ይሆናል

ሊሆኑ የሚችሉ ትርጉሞች 1) “በአስጸያፊነታችሁ ምክንያት ሁላችሁንም እቀጣችኋለሁ” ወይም 2) “ጣዖታትን ማምለካችሁን እስከ ቀጠላችሁ ድረስ ይህ ይደርስባችኋል” የሚሉት ናቸው።

እኔ እግዚአብሔር መሆኔን ዕወቁ

እግዚአብሔር ሰዎች እርሱ እግዚአብሔር መሆኑን ያውቃሉ ብሎ በሚናገርበት ጊዜ እርሱ ፍጹም ኃይልና ሥልጣን ያለው ብቸኛው እውነተኛ አምላክ መሆኑን ሰዎች ያውቃሉ ማለቱ ነው። አ.ት፡ “እውነተኛው አምላክ እኔ እግዚአብሔር መሆኔን ተረዱ” ወይም “ፍጹም ኃይልና ሥልጣን ያለኝ እኔ እግዚአብሔር መሆኔን ተገንዘቡ”