am_tn/ezk/05/15.md

2.3 KiB

በቁጣና በንዴት

“ቁጣ” እና “ንዴት” የሚሉት ቃላት መሠረታዊ ትርጉማቸው አንድ ነገር ሲሆን እግዚአብሔር በጣም ስለመቆጣቱ አጽንዖት ይሰጣሉ። አ.ት፡ “በጣም ስለተቆጣሁሽ”

የረሃብን አሰቃቂ ፍላጻዎች በአንቺ ላይ እወረውራለሁ

“ፍላጻዎች” የሚለው ቃል ሕዝቡ ለረጅም ጊዜ ምግብ በሚያጡበት ጊዜ የሚሰማቸውን ብርቱ ህመም የሚያመለክት ፈሊጣዊ አነጋገር ነው። አ.ት፡ “የጽኑ ረሃብ ህመም እንዲሰማችሁ አደርጋለሁ” (ፈሊጣዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)

ረሃብን አበዛባችኋለሁ

“ረሃባችሁን አስከፊ አደርገዋለሁ” ወይም “ረሃባችሁ ለረጅም ጊዜ እንዲቆይ አደርጋለሁ” ወይም “የምትበሉት ከጊዜ ወደ ጊዜ እያነሰባችሁ እንደሚሄድ እርግጠኛ ሁኑ”

የእንጀራችሁን በትር መስበር

“በትር” ሰዎች ለድጋፍ የሚመረኮዙት ነገር ነው። ይህ ሐረግ ሕዝቡ የተማመነበትን የምግብ አቅርቦት የማስወገድ ዘይቤአዊ አነጋገር ነው። “የእንጀራ በትር” በሕዝቅኤል 4፡16 ላይ እንዴት እንደ ተተረጎመ ተመልከት። አ.ት፡ “የምግብ አቅርቦታችሁን አቋርጣለሁ” (ዘይቤአዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)

በመካከላችሁ ቸነፈርና ደም ያልፋል

በሽታና አስከፊ ሞት በከተማው ውስጥ በመዘዋወር ያገኙትን ሁሉ በሚገድሉ ወታደሮች ተመስለዋል። አ.ት፡ “ብዙ ሰዎች በበሽታ ይሞታሉ፣ ሌሎች ብዙዎች ደግሞ በጦርነት ይሞታሉ” (ሰውኛ የሚለውን ተመልከት)

በእናንተ ላይ ሰይፍን አመጣለሁ

“ሰይፍ” የሚለው ቃል ሰይፍን በመጠቀም ሰዎችን የሚገድሉትን ወታደሮች የሚያመለክት ፊሊጣዊ አነጋገር ነው። አ.ት፡ “እኔ ራሴ ወታደሮች መጥተው እንዲገድሏችሁ አደርጋለሁ” (ፈሊጣዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)