am_tn/ezk/05/09.md

1.2 KiB

ያላደረግሁትንና ዳግመኛም የማላደርገውን

“ቀድሞ ያላደረግሁትንና ዳግመኛ በተመሳሳይ መንገድ የማላደርገውን” ወይም “ቀድሞ ከቶ ያላደረግሁትንና ዳግመኛም ከቶ የማላደርገውን”።

በአስጸያፊ ተግባሮችሽ ሁሉ ምክንያት

“በምታደርጊያቸው አስጸያፊ ነገሮች ሁሉ ምክንያት”። ሕዝቡ ጣዖታትንና ሐሰተኞች አማልክትን ያመልኩ ስለ ነበር እግዚአብሔር ተቆጥቷል።

በመካከልሽ አባቶች ልጆቻቸውን ይበላሉ፣ ወንዶቹ ልጆችም አባቶቻቸውን ይበላሉ

ሕዝቅኤል የሚነግራቸው ምናልባት ሕዝቡ የሚበሉትን ምግብ በሚያጡበት ጊዜ በእርግጠኝነት ምን ሊሆን እንዳለ ነው።

ፍርድን እፈጽምብሻለሁ

“እፈርድብሻለሁ” ወይም “የከፋ ቅጣት እቀጣሻለሁ”

የቀራችሁትን ሁሉ በተለያየ አቅጣጫ እበትናችኋለሁ

“የቀራችሁትን ሁሉ ወደ ተለያዩ ቦታዎች እንድትሄዱ አስገድዳችኋለሁ”