am_tn/ezk/05/03.md

2.8 KiB

ነገር ግን ውሰድ … ከዚያም ውሰድ

ሕዝቅኤል ጸጉሩንና ጺሙን በተላጨ ጊዜ ጸጉሩን ከማቃጠሉ በፊት ይህንን ማድረግ ነበረበት (ሕዝቅኤል 5፡1-2)። እነዚህን ቁጥሮች ከእነዚያ ቁጥሮች በፊት ማድረግ ይኖርብህ ይሆናል። “ይሁን እንጂ ጸጉርህንና ጺምህን በምትላጭበት ጊዜ ከማቃጠልህ በፊት . . . ውሰድ። ከዚያም ጸጉሩን በንፋስ ላይ ከበተንከው በኋላ ውሰድ” (የሁነቶች ቅደም ተከተል እና የቁጥር መሸጋገሪያ የሚለውን ተመልከት)

ከእነርሱ ላይ ጥቂት ቁጥር ያለውን ጸጉር

“ከክምሩ ላይ ጥቂት ጸጉሮችን”

በአንድ ላይ እሰራቸው

“እነርሱን” የሚለው ቃል የሚያመለክተው ጸጉሮቹን ነው። ሊሆኑ የሚችሉ ትርጉሞች 1) ጸጉሮቹ ሕዝቅኤል ሊያስራቸው እስኪችል ድረስ ረጅም ነበሩ ወይም 2) ሕዝቅኤል ጸጉሮቹን በአንድ ላይ መስፋት ወይም ማጣበቅ ነበረበት 3) ሕዝቅኤል ጸጉሮቹን በልብስ እጥፋት ውስጥ ማስቀመጥ ነበረበት የሚሉት ናቸው።

በልብስህ እጥፋት

ሊሆኑ የሚችሉ ትርጉሞች 1) “በክንድህ ላይ ያለ ልብስ” (“የልብስህ እጅጌዎች”) ወይም 2) “የልብስህ ዘርፍ” (“የልብስህ ጠርዝ”) ወይም 3) መታጠቂያ ላይ የሚሸጎጥበት የልብስ እጥፋት የሚሉት ናቸው።

እሳት ከዚያ ወደ እስራኤል ቤት ሁሉ ይወጣል

“እሳት ከዚያ ይስፋፋል፣ የእስራኤልን ሕዝብ በሙሉ ያቃጥላል”። እስራኤል በዚያ ቤት ውስጥ የሚኖሩ ቤተሰቦች የሆኑ ያህል (ይሁን እንጂ በዚያን ጊዜ ከቤቱ ውጭ ነበሩ) እግዚአብሔር በቤቱና በእስራኤል ሕዝብ ላይ እሳት በመለኮስ እስራኤልን እንዴት እንደሚቀጣት ይናገራል። (ዘይቤአዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)

የእስራኤል ቤት

“ቤት” የሚለው ቃል በቤቱ ውስጥ የሚኖሩትን ቤተሰቦች የሚያመለክት ፈሊጣዊ አነጋገር ነው፤ በመሆኑም፣ ይህ ከረጅም ዓመታት ጀምሮ ያሉትን የያዕቆብን ዘሮች፣ እስራኤላውያንን ያመለክታል። ይህንን በሕዝቅኤል 3፡1 ላይ እንዴት እንደ ተረጎምከው ተመልከት። አ.ት፡ “እስራኤላውያንን” ወይም “የእስራኤል ሕዝብ ወገን” (ፈሊጣዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)