am_tn/ezk/05/01.md

1.5 KiB

የሰው ልጅ

“የሰብዓዊ ፍጡር ልጅ” ወይም “ከሰው የተወለደ ልጅ”። ሕዝቅኤል ሰው ብቻ መሆኑን አፅንኦት ለመስጠት እግዚአብሔር ሕዝቅኤልን እንዲህ በማለት ይጠራዋል። እግዚአብሔር ዘላለማዊና ኃያል ነው፣ ሰዎች ግን አይደሉም። ይህንን በሕዝቅኤል 2፡1 ላይ እንዴት እንደ ተረጎምከው ተመልከት። አ.ት፡ “ሟች ሰው” ወይም “ሰው”

የጸጉር ቆራጭ ምላጭ

“ጸጉር ለመቁረጥ የሚያገለግል ምላጭ”

በራስህና በጺምህ ላይ ምላጭ አሳልፍ

“ጸጉርህንና ጺምህን ተላጨው” ወይም “ከራስህ ላይ ጸጉርህን፣ ከፊትህም ላይ ጺምህን አስወግድ”

አንድ ሦስተኛውን አቃጥለው

“ከጸጉርህ አንድ ሦስተኛውን አቃጥለው” )

መካከል

መካከል

የከበባዎቹ ቀናት በሚያበቁበት ጊዜ

“የኢየሩሳሌም የከበባዎቹ ቀናት ባበቃ ጊዜ” ወይም “ኢየሩሳሌም እንዴት በከበባ ስር እንደምትወድቅ የምታሳይበት ቀናት በሚያበቁበት ጊዜ”

አንድ ሦስተኛውን ጸጉር ውሰድ

“ከሦስቱ የጸጉር ክምሮች አንደኛውን ውሰድ”

እርሱን በከተማይቱ ዙሪያ ሁሉ በሰይፍ ምታው

“እርሱን በከተማው ሁሉ ላይ በሰይፍህ ምታው”