am_tn/ezk/04/16.md

2.2 KiB

እነሆ

“ተመልከት” ወይም “ስማ” ወይም “የምነግርህን ልብ በል”

በኢየሩሳሌም የእንጀራን በትር እሰብራለሁ

“የኢየሩሳሌምን የምግብ አቅርቦት አቆማለሁ”

የእንጀራ በትር

አቅርቦቱ በትር ተብሎ ተጠርቷል፤ ምክንያቱም አንዳንድ ሰዎች መንገድ ለመሄድና ሥራቸውን ለመሥራት ምርኩዝ እንደሚፈልጉ ሁሉ ሰዎች በሕይወት ለመኖር ምግብ ይፈልጋሉ። እንጀራ ሁሉንም ዓይነት ምግብ ይወክላል። አ.ት፡ “የምግብ አቅርቦት” (ዘይቤአዊ አነጋገር እና Synecdoche የሚለውን ተመልከት)

እንጀራን በስጋት መጥነው ይበላሉ

እንጀራውን ለምን እንደሚመጥኑት ግልጽ ማድረግ ያስፈልግህ ይሆናል። “ላይበቃቸው እንደሚችል በማሰብ እንጀራቸውን በጥንቃቄ ይከፋፍላሉ”

መመጠን

ለብዙ ሰዎች የማይበቃ ሲሆን የአንድን ነገር አነስተኛ መጠን መስጠት ነው።

እርሱን በመንቀጥቀጥ መመጠን

“መደንገጥ” የሚለው ቃል የመፍራት ዘይቤአዊ አነጋገር ሲሆን “መንቀጥቀጥ” ፍርሃትን ይወክላል። አ.ት፡ “እየደነገጡ መመጠን” ወይም “እየፈሩ መመጠን” (ዘይቤአዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)

እያንዳንዱ ሰው በወንድሙ ተስፋ ይቆርጣል፣ መንምኖም ይጠፋል

ሊሆኑ የሚችሉ ትርጉሞች፣ 1) “እያንዳንዱ ወንድሙ ምን ያህል ምግብ በመብላት መንምኖ እንደሚጠፋ በማየት ይጨነቃል”

መንምኖ መጥፋት

“መንምኖ መጥፋት” የሚለው ሐረግ በአብዛኛው ጥቅም ላይ የሚውለው ለሥጋ ወይም ለሚበሰብስ እንጨት ነው። እዚህ ጋ በዘይቤአዊ አነጋገር ክፉ ሰዎች ምግብ ስለሌላቸው እንደሚከሱና እንደሚሞቱ ያሳያል። (ዘይቤአዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)