am_tn/ezk/04/14.md

1.5 KiB

ኦ! ጌታ እግዚአብሔር

“ጌታ እግዚአብሔር ሆይ፣ ይህንን ማድረግ አይገባኝም”። ጌታ እንዲያደርግ ባዘዘው ነገር ሕዝቅኤል በጣም ተረብሿል።

ጌታ እግዚአብሔር

ይህንን በሕዝቅኤል 2፡4 ላይ እንዴት እንደተረጎምከው ተመልከት። እዚህ ጋ ሕዝቅኤል እየተናገረ ያለው ለጌታ ነው።

የተበከለ ሥጋ ወደ አፌ ከቶ ገብቶ አያውቅም

“የተበከለ ሥጋ ከቶ በልቼ አላውቅም”

የተበከለ ሥጋ

“አስቀያሚ፣ እርኩስ ሥጋ”። ይህ በበሽታ ወይም በእርጅና ምክንያት ከሞተ ወይም በሌላ እንስሳ ከተገደለ እንስሳ የመጣ እርኩስ ሥጋን ያመለክታል።

ተመልከት

“ስማ” ወይም “አሁን ለምነግርህ ጠቃሚ ነገር ትኩረት ስጥ”

ሰጥቼሃለሁ

“እንድትጠቀምበት እፈቅድልሃለሁ”

የከብት ፍግ

ከከብቶች የሚገኝ ኩበት። የአንተ ቋንቋ ይህንን የሚገልጽበት የትህትና አገላለጽ ይኖረው ይሆናል።

የሰው ሰገራ

ከሰው የሚወጣ ጠጣር ሰገራ። የአንተ ቋንቋ ይህንን የሚገልጽበት የትህትና አገላለጽ ይኖረው ይሆናል። ይህንን በሕዝቅኤል 4፡12 ላይ እንዴት እንደ ተረጎምከው ተመልከት።