am_tn/ezk/04/06.md

3.1 KiB

በእነዚህ ቀናት

የእስራኤል መንግሥት እንደምትከበብ ለማመልከት ሕዝቅኤል በግራ ጎኑ የሚተኛባቸው ቀናት

ኃጢአትን ትሸከማለህ

ሊሆኑ የሚችሉ ትርጉሞች 1) “ስለ ኃጢአት በደለኛ ትሆናለህ” ወይም 2) “ስለ ኃጢአት ተቀጣለህ”። ከእነዚህ ትርጉሞች ሁለቱም ክፍት በሆነው ተለዋዋጭ የመጽሐፍ ቅዱስ ትርጉም ላይ እንደተመለከተው በ”ምልክታዊነት” ይገለጻል። እነዚህን ቃላት በሕዝቅኤል 4፡4 ላይ እንዴት እንደ ተረጎምከው ተመልከት።

የይሁዳ ቤት

“ቤት” የሚለው ቃል በቤቱ ውስጥ የሚኖሩትን ቤተሰቦች የሚያመለክት ፈሊጣዊ አነጋገር ነው፤ በመሆኑም፣ ይህ ከረጅም ዓመታት ጀምሮ ያሉትን የይሁዳን ዘሮች ያመለክታል። እነዚህን ቃላት በሕዝቅኤል 3፡1 ላይ እንዴት እንደተረጎምካቸው ተመልከት። አ.ት፡ “የይሁዳ ሕዝብ ወገን” ወይም “የይሁዳ ሕዝብ” (ፈሊጣዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)

ለእያንዳንዱ ዓመት አንድ ቀን መድቤልሃለሁ

“ይህንን አንድ ቀን እኔ ለምቀጣቸው ለእያንዳንዱ ዓመት እንድታደርገው አደርግሃለሁ”

ፊትህን በተከበበችው በኢየሩሳሌም አቅጣጫ አድርግ

ይህ በኢየሩሳልም ምሳሌ ላይ አፍጥጦ እንዲመለከት የተሰጠ ትዕዛዝ ኢየሩሳሌም የመቀጣቷ ምልክት ነው። ተመሳሳዩን ሐረግ በሕዝቅኤል 4፡3 ላይ እንዴት እንደ ተረጎምከው ተመልከት። አ.ት፡ “በተከበበችው በኢየሩሳሌም ከተማ ላይ አፍጥጥባት” ወይም “ጉዳት ይደርስባታልና በተከበበችው በኢየሩሳሌም ከተማ ላይ አፍጥጥባት”

ፊትህን አቅና

እዚህ ጋ “ፊት” ፍላጎትን ወይም አትኩሮትን የሚወክል ፈሊጣዊ አነጋገር ሲሆን “ፊትህን አቅና” የሚያመለክተው በአንድ ነገር ላይ በቀጥታ ማተኮርን ነው። (ፈሊጣዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)

በእርሱ ላይ ትንቢት ተናገር

“በኢየሩሳሌም ላይ ሊመጡ ስላሉት መጥፎ ነገሮች ትንቢት ተናገር”

እይ

“ተመልከት” ወይም “አድምጥ” ወይም “የምነግርህን ልብ በል”

ማሰሪያ እጥልብሃለሁ

ማሰሪያ አንድን ሰው ከመንቀሳቀስ የሚገድቡ ገመዶች ወይም ሰንሰለቶች ናቸው። “ማሰሪያ” የሚለው ቃል እግዚአብሔር ሕዝቅኤልን ያሰረበትን አንዳች ነገር አመልካች ዘይቤአዊ አነጋገር ወይስ በቀጥታ የሚታይ ገመድ ተጠቅሞ እንደሆነ ግልጽ አይደለም። (ዘይቤአዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)