am_tn/ezk/04/04.md

2.1 KiB

የእስራኤልን ቤት ኃጢአት በእርሱ ላይ አኑርበት

ሊሆኑ የሚችሉ ትርጉሞች፣ 1) “ስለ እስራኤላውያኑ ኃጢአት ቅጣቱን በምልክትነት ተሸከም” ወይም 2) “በኃጢአታቸው ምክንያት በጎንህ በመተኛት መከራን ተቀበል” የሚሉት ናቸው።

የእስራኤል ቤት

“ቤት” የሚለው ቃል በቤቱ ውስጥ የሚኖሩትን ቤተሰቦች የሚያመለክት ፈሊጣዊ አነጋገር ነው፤ በመሆኑም፣ ይህ ከረጅም ዓመታት ጀምሮ ያሉትን የያዕቆብን ዘሮች፣ እስራኤላውያንን ያመለክታል። ይህንን በሕዝቅኤል 3፡1 ላይ እንዴት እንደ ተረጎምከው ተመልከት። አ.ት፡ “እስራኤላውያንን” ወይም “የእስራኤል ሕዝብ ወገን” (ፈሊጣዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)

ኃጢአታቸውን ትሸከማለህ

ሊሆኑ የሚችሉ ትርጉሞች 1) “በኃጢአታቸው ምክንያት አንተ በደለኛ ትሆናለህ” ወይም 2) “በኃጢአታቸው ምክንያት ትቀጣለህ”። ከእነዚህ ትርጉሞች ሁለቱም ክፍት በሆነው ተለዋዋጭ የመጽሐፍ ቅዱስ ትርጉም ላይ እንደተመለከተው በ”ምልክታዊነት” ይገለጻል።

የእስራኤልን ቤት በመቃወም ተጋደም

“የእስራኤልን መንግሥት በቁጣ እያየህ ተጋደም”

የሚቀጡባቸውን ዓመታት እንዲወክል አንድን ቀን የምመድብልህ እኔው ራሴ ነኝ

“በምቀጣቸው ዓመታት ቁጥር ልክ ተመሳሳይ ቀናትን በጎንህ እንድትተኛ የማዝህ እኔው ራሴ ነኝ”

በእያንዳንዱ በሚቀጡበት ዓመት

ሊሆኑ የሚችሉ ትርጉሞች 1) በየዓመቱ ስለ ኃጢአታቸው ይቀጣሉ ወይም 2) በየዓመቱ ኃጢአትን ሠርተዋል የሚሉት ናቸው።

390 ቀናት

“ሦስት መቶ ዘጠና ቀናት” (ቁጥሮች የሚለውን ተመልከት)