am_tn/ezk/04/01.md

3.3 KiB

የሰው ልጅ

“የሰብዓዊ ፍጡር ልጅ” ወይም “ከሰው የተወለደ ልጅ”። ሕዝቅኤል ሰው ብቻ መሆኑን አፅንኦት ለመስጠት እግዚአብሔር ሕዝቅኤልን እንዲህ በማለት ይጠራዋል። እግዚአብሔር ዘላለማዊና ኃያል ነው፣ ሰዎች ግን አይደሉም። ይህንን በሕዝቅኤል 2፡1 ላይ እንዴት እንደ ተረጎምከው ተመልከት። አ.ት፡ “ሟች ሰው” ወይም “ሰው”

የኢየሩሳሌምን ከተማ ቅረጽ

ሕዝቅኤል ሥዕል ሊሥል እንደሆነ ግልጽ ማድረግ ይኖርብህ ይሆናል። አ.ት፡ “የኢየሩሳሌምን ከተማ ሥዕል ሣል”

በእርሷ ላይ ከበባን አድርግባት

“ከተማይቱን ለመማረክ ክበባት”

በእርሷ ላይ ምሽግን ሥራባት

“በእርሷ ላይ ጠንካራ ግንብ ሥራባት”። ሕዝቡ ከተማይቱን ትቶ እንዳይወጣ ግንቡ ያግደዋል።

በእርሷ ላይ የማጥቂያ መሰላል አቁምባት

“ጠላት እንዲገባባት በስተውጪዋ መሰላል ሥራባት”። ኢየሩሳሌም በውስጧ የሚኖረውን ሕዝብ ለመከላከል በዙሪያዋ ቅጥር ነበራት። ጠላት ወደ ውስጥ መግባት የሚችለው በቅጥሩ ላይ መዝለል የሚያስችለው መሰላል ከኖረው ብቻ ነበር።

በዙሪያዋ የግንብ ማፍረሻ መሣሪያ አኑርባት

“ሰዎች በሮቹን ሰብረው ወደ ውስጥ መግባት እንዲችሉ ትላልቅ ግንዶችን በዙሪያዋ አስቀምጥ”። “ግንብ ማፍረሻ መሣሪያዎች” ሰብረው ወደ ውስጥ መግባት እንዲቻላቸው በውትድርና ውስጥ ያሉ በርካታ ወንዶች አንሥተው ግንቡን ወይም በሩን የሚመቱባቸው ረጃጅም ዛፎች ወይም ምሶሶዎች ናቸው።

ፊትህን በእርሱ አቅጣጫ አዙር

ይህ በከተማይቱ ምሳሌ ላይ አፍጥጦ እንዲመለከት የተሰጠ ትዕዛዝ ከተማይቱ የመቀጣቷ ምልክት ነው። አ.ት፡ “በከተማይቱ ላይ አፍጥጥባት” ወይም “ጉዳት ይደርስባታልና በከተማይቱ ላይ አፍጥጥባት”

ፊትህን አቅና

እዚህ ጋ “ፊት” ፍላጎትን ወይም አትኩሮትን የሚወክል ፈሊጣዊ አነጋገር ሲሆን “ፊትህን አቅና” የሚያመለክተው በአንድ ነገር ላይ በቀጥታ ማተኮርን ነው። (ፈሊጣዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)

የእስራኤል ቤት

“ቤት” የሚለው ቃል በቤቱ ውስጥ የሚኖሩትን ቤተሰቦች የሚያመለክት ፈሊጣዊ አነጋገር ነው፤ በመሆኑም፣ ይህ ከረጅም ዓመታት ጀምሮ ያሉትን የያዕቆብን ዘሮች፣ እስራኤላውያንን ያመለክታል። ይህንን በሕዝቅኤል 3፡1 ላይ እንዴት እንደ ተረጎምከው ተመልከት። አ.ት፡ “እስራኤላውያንን” ወይም “የእስራኤል ሕዝብ ወገን” (ፈሊጣዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)