am_tn/ezk/03/22.md

1.2 KiB

የእግዚአብሔር እጅ

“እጅ” የሚለው ቃል አብዛኛውን ጊዜ የአንድን ሰው ኃይል ወይም ተግባር ለማመልከት ጥቅም ላይ ውሏል። አ.ት፡ “የእግዚአብሔር ኃይል” (ፈሊጣዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)

የእግዚአብሔር ክብር

ይህንን በሕዝቅኤል 1:28 ላይ እንዴት እንደ ተረጎምከው ተመልከት።

የኮቦር ቦይ

ይህ ከለዳውያን የእትክልት ቦታቸውን ለማጠጣት ቆፍረውት የነበረ ወንዝ ነው። ይህንን በሕዝቅኤል 1፡1 ላይ እንዴት እንደ ተረጎምከው ተመልከት።

በግንባሬ ተደፋሁ

“በምድር ላይ ሰገድሁ” ወይም “በምድር ላይ ተጋደምኩ”። ሕዝቅኤል የወደቀው በአደጋ ምክንያት አይደለም። እርሱ በምድር ላይ የወደቀው ለእግዚአብሔር ያለውን አክብሮትና ፍርሐት ለማሳየት ነው። ይህንን በሕዝቅኤል 1፡28 ላይ እንዴት እንደ ተረጎምከው ተመልከት። (የአነጋገር ዘይቤ የሚለውን ተመልከት)