am_tn/ezk/03/20.md

1.2 KiB

በፊቱ ማሰናከያ ማስቀመጥ

ሊሆኑ የሚችሉ ትርጉሞች፣ 1) “ክፉ ነገር እንዲደርስበት አድርግ” ወይም 2) “በግልጽ ኃጢአትን እንዲሠራ አድርገው” የሚሉት ናቸው። (ዘይቤአዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)

በኃጢአቱ ይሞታል

“እንደ ኃጢአተኛ ይሞታል” ወይም “እኔን ስላልታዘዘኝ እንደ በደለኛ ሰው ይሞታል”

ደሙን ከእጅህ እፈልጋለሁ

ይህ አንድን ሰው በግድያ ወንጀል በኃላፊነት ወይም በበደለኝነት ስለመያዝ የተነገረ የአነጋገር ዘይቤ ነው። ይህንን በሕዝቅኤል 3፡18 ላይ እንዴት እንደተረጎምከው ተመልከት። አ.ት፡ “አንተ ራስህ እንደገደልከው ቆጥሬ እፈርድብሃለሁ” (የአነጋገር ዘይቤ የሚለውን ተመልከት)

ማስጠንቀቂያ ተሰጥቶታልና

ይህ በአድራጊ ድምፅ ሊተረጎም ይችላል። አ.ት፡ “አስጠንቅቀኸዋልና” (አድራጊ ወይም ተደራጊ ድምፅ የሚለውን ተመልከት)