am_tn/ezk/03/16.md

2.4 KiB

የእግዚአብሔር ቃል መጣ

ይህ እግዚአብሔር ለነቢያቱ ወይም ለሕዝቡ አንድን ነገር ለማስታወቅ የሚጠቀምበት የአነጋገር ዘይቤ ነው። አ.ት፡ “እግዚአብሔር ይህንን መልዕክት ተናገረ” ወይም “እነዚህን ቃላት እግዚአብሔር ተናገረ” (የአነጋገር ዘይቤ የሚለውን ተመልከት)

ጠባቂ

የአንድ ከተማ ሕዝብ እንዲዘጋጅና እንዲድን ጠባቂው ጠላት በመምጣት ላይ መሆኑን እንደሚያስጠነቅቅ ሁሉ ሕዝቅኤል የእስራኤልን ሕዝብ እንዲያስጠነቅቅ እግዚአብሔር ነግሮታል። (ዘይቤአዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)

የእስራኤል ቤት

“ቤት” የሚለው ቃል በቤቱ ውስጥ የሚኖሩትን ቤተሰቦች የሚያመለክት ፈሊጣዊ አነጋገር ነው፤ በመሆኑም፣ ይህ ከረጅም ዓመታት ጀምሮ ያሉትን የያዕቆብን ዘሮች፣ እስራኤላውያንን ያመለክታል። ይህንን በሕዝቅኤል 3፡1 ላይ እንዴት እንደ ተረጎምከው ተመልከት። አ.ት፡ “እስራኤላውያንን” ወይም “የእስራኤል ሕዝብ ወገን” (ፈሊጣዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)

ኃጢአተኛው በሕይወት ይኖር ዘንድ ስለ ክፉ ሥራው ማስጠንቀቂያ

ኃጢአተኛው ክፉ ሥራ መሥራቱን ማቆም እንዳለበት ግልጽ ማድረግ ይኖርብሃል። አ.ት፡ “ኃጢአተኛው በሕይወት ይኖር ዘንድ ክፉ ሥራውን ከመሥራት እንዲያቆም ማስጠንቀቂያ”

ኃጢአተኛው

“ክፉ ሕዝብ”

ደሙን ከእጅህ እፈልጋለሁ

ይህ አንድን ሰው በግድያ ወንጀል በኃላፊነት ወይም በበደለኝነት ስለመያዝ የተነገረ የአነጋገር ዘይቤ ነው። አ.ት፡ “አንተ ራስህ እንደገደልከው ቆጥሬ እፈርድብሃለሁ” (የአነጋገር ዘይቤ የሚለውን ተመልከት)

ከኃጢአቱ ወይም ከክፉ ሥራው አይመለስም

“ከክፉ ሥራው” የሚለው ሐረግ ትርጉሙ “ከኃጢአቱ” ከሚለው ጋር ተመሳሳይ ነው። አ.ት፡ “ክፉ ነገሮችን ማድረጉን አያቆምም”