am_tn/ezk/03/12.md

1.7 KiB
Raw Permalink Blame History

“የእግዚአብሔር ክብር ከስፍራው ይባረክ!” የሚል ታላቅ የመሬት መንቀጥቀጥ ድምፅ ከበስተኋላዬ ሰማሁ

አንዳንድ ትርጉሞች “ስፍራ … ይባረክ!” የሚሉትን ቃላት “ታላቅ የመሬት መንቀጥቀጥ” የተናገረው አድርገው ይወስዳሉ፤ “’የእግዚአብሔር ክብር ከስፍራው ይባረክ! የሚለውን ታላቅ የምድር መንቀጥቀጥ ድምፅ ከበስተኋላዬ ሰማሁ”። ሌሎች የምድር መንቀጥቀጡን ድምፅ የእግዚአብሔር ክብር ከስፍራው ሲለቅ የነበረው ድምፅ አድርገው ይረዳሉ፣ “የእግዚአብሔር ክብር ስፍራውን ሲለቅ ከበስተኋላዬ ታላቅ የምድር መንቀጥቀጥ ድምፅ ሰማሁ”።

ታላቅ የመሬት መንቀጥቀጥ ድምፅ

ድምፁ ከመሬት መንቀጥቀጥ፣ እንደ መሬት መንቀጥቀጥ ከፍ ካለ ድምፅ፣ ወይም ከክንፎችና ከመንኩራኩሮች መጥቶ እንደሆን ግልጽ አይደለም። አ.ት፡ “ታላቅ የመሬት መንቀጥቀጥ ድምፅን የሚመስል ድምፅ” ወይም “የሚናገርን ድምፅ፤ ታላቅ የመሬት መንቀጥቀጥ ድምፅን የሚመስል ድምፅ” ወይም “ከፍ ያለ የጉርምርምታ ድምፅ”

የእግዚአብሔር ክብር

ይህንን በሕዝቅኤል 1፡28 ላይ እንዴት እንደተረጎምከው ተመልከት።

ታላቅ የመሬት መንቀጥቀጥ ድምፅ

“እንደ መሬት መንቀጥቀጥ ድምፅ ያለ ከፍተኛ፣ ጥልቅና ኃይለኛ የጉርምርምታ ድምፅ”