am_tn/ezk/03/04.md

2.5 KiB

ተናገረኝ

የአንተ ቋንቋ ተናጋሪውን መለየት ካለበት “አንድ ሰውን የሚመስል” በማለት ቢለየው ይመረጣል (ሕዝቅኤል 1፡26)። እርሱ “መንፈስ ቅዱስ” አልነበረም።

የእስራኤል ቤት

ይህ በቤቱ ውስጥ የሚኖሩትን ቤተሰቦች የሚያመለክት ፈሊጣዊ አነጋገር ነው፤ በመሆኑም፣ ይህ ከረጅም ዓመታት ጀምሮ ያሉትን የያዕቆብን ዘሮች፣ እስራኤላውያንን ያመለክታል። ይህንን በሕዝቅኤል 3፡1 ላይ እንዴት እንደ ተረጎምከው ተመልከት። አ.ት፡ “እስራኤላውያንን” ወይም “የእስራኤላውያንን የሕዝብ ወገን” (ፈሊጣዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)

እንግዳ ንግግር ወይም አስቸጋሪ ቋንቋ

“እንግዳ ወይም አስቸጋሪ ቋንቋ የሚናገር”

እንግዳ ንግግር ወደሚናገሩ ወደ ብዙ ሰዎች አይደለም

“ሕዝባቸው እንግዳ ቋንቋ ወደሚናገር ብርቱ ሕዝብ አልካሁህም”

ወደ እነርሱ ብልክህ ኖሮ ይሰሙህ ነበር

ይህ ሊሆን የሚችል፣ ነገር ግን ያልሆነ መላ ምታዊ ሁኔታ ነው። እግዚአብሔር የሕዝቅኤልን ቋንቋ መረዳት ወደማይችሉ ሕዝቦች አልላከውም።

ወደ እነርሱ ብልክህ ኖሮ

“እነርሱ” የሚለው ቃል ከእስራኤል ሌላ ብርቱ የሆነን ሕዝብ ያመለክታል።

ግንባረ ጠንካራ እና ልበ ደንዳና

በመሠረቱ የሁለቱም ትርጉም ተመሳሳይ ነው። አ.ት፡ “በጣም አመፀኞች” ወይም “በጣም እልኸኞች”

ግንባረ ጠንካራ

ይህ የአነጋገር ዘይቤ ነው። አ.ት፡ “ለለውጥ ፈቃደኛ አለመሆን” (የአነጋገር ዘይቤ የሚለውን ተመልከት)

ልበ ደንዳና

ይህ ሐረግ ሕዝቡ እግዚአብሔርን እንደተቋቋሙትና ሊታዘዙት ፈቃደኞች አለመሆናቸውን ይጠቁማል። ሕዝቡ ለማድረግ የሚፈልጉትን የሚወስኑበትን በአካል ውስጥ የሚገኘውን ስፍራ ለመገለጽ ልብ ጥቅም ላይ ውሏል። ይህንን በሕዝቅኤል 2፡4 ላይ እንዴት እንደ ተረጎምከው ተመልከት። (ዘይቤአዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)