am_tn/ezk/03/01.md

1.9 KiB

ተናገረኝ

“እርሱ” የሚለው ቃል የሚያመለክተው “አንድ ሰው የሚመስል” የተባለለትን ነው (ሕዝቅኤል 1፡26)

የሰው ልጅ

“የሰብዓዊ ፍጡር ልጅ” ወይም “ከሰው የተወለደ ልጅ”። ሕዝቅኤል ሰው ብቻ መሆኑን አፅንኦት ለመስጠት እግዚአብሔር ሕዝቅኤልን እንዲህ በማለት ይጠራዋል። እግዚአብሔር ዘላለማዊና ኃያል ነው፣ ሰዎች ግን አይደሉም። ይህንን በሕዝቅኤል 2፡1 ላይ እንዴት እንደተረጎምከው ተመልከት። አ.ት፡ “ሟች ሰው” ወይም “ሰው”

ያገኘኸውን

ይህ የሚያመለክተው እግዚአብሔር እየሰጠው ያለውን የመጽሐፍ ጥቅልል ነው (ሕዝቅኤል 2፡9ን ተመልከት)

የእስራኤል ቤት

ይህ በቤቱ ውስጥ የሚኖሩትን ቤተሰቦች የሚያመለክት ፈሊጣዊ አነጋገር ነው፤ በመሆኑም፣ ይህ ከረጅም ዓመታት ጀምሮ ያሉትን የያዕቆብን ዘሮች፣ እስራኤላውያንን ያመለክታል። አ.ት፡ “እስራኤላውያንን” ወይም “የእስራኤላውያንን የሕዝብ ወገን” (ፈሊጣዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)

ያ ጥቅልል

ብዙ ትርጉሞች “ጥቅልሉ” ወይም “ይህ ጥቅልል” የሚል አላቸው።

በዚህ ጥቅልል ሆድህን መግበው፣ ጨጓራህንም ሙላው

“ሆድ” የሚለው ቃል ሰዎች ከውጭ ሊያዩት የሚችሉትን የሰውነት ክፍል ያመለክታል። “ጨጓራ” የሚለው ቃል ደግሞ በሆድ ውስጥ ያለውን ውስጣዊ ብልት ያመለክታል።

እርሱም እንደ ማር ይጣፍጥ ነበር

ማር ይጣፍጣል፣ ጥቅልሉም ይጣፍጥ ነበር።