am_tn/ezk/02/09.md

1.6 KiB

አንድ እጅ ወደ እኔ ተዘርግቶ ነበር

ይህ፣ 1) በሰማያት ውስጥ ያለ አንድ ሰው እጁን ወደ ሕዝቅኤል ዘርግቶለታል፤ ሕዝቅኤል ማየት የቻለው ከእጁ እስከ ክርኑ ወይም እስከ ትከሻው ያለውን ብቻ ነው፣ ወይም 2) “የሰው ልጅ የሚመስለው” እጁን ዘርግቷል (ሕዝቅኤል 1፡26)።

የተጻፈበት ጥቅልል

“ጽሑፍ ያለበት ጥቅልል”

ዘረጋው

በውስጠ ታዋቂ ያለው “እርሱ” የሚያመለክተው “የሰው ልጅ የሚመስለውን” ነው (ሕዝቅኤል 1፡26)።

በፊት ለፊቱና በጀርባው ላይ በሁለቱም በኩል ተጽፎበት ነበር

ይህ በአድራጊ ድምፅ ሊተረጎም ይችላል። አ.ት፡ “አንድ ሰው በፊት ለፊቱና በስተጀርባው በሁለቱም በኩል ጽፎበት ነበር” (አድራጊ ወይም ተደራጊ ድምፅ የሚለውን ተመልከት)

በላዩ ላይ ሙሾ፣ ለቅሶና ዋይታ ተጽፎበት ነበር

ይህ የነገር ስም የሆኑትን “ሙሾ”፣ “ለቅሶ”፣ እና “ዋይታ”ን ለማስቀረት እንደገና መነገር ይችላል። አ.ት፡ “እነዚህ ሰዎች እንደሚያሟሹ፣ አንድ የሚወዱት ቢሞትባቸው እንደሚሆኑት ሁሉ እንደሚያዝኑና የከፋ ነገር እንደሚደርስባቸው አንድ ሰው ጽፎበት ነበር” (የነገር ስም የሚለውን ተመልከት)