am_tn/ezk/02/06.md

1.8 KiB

የሰው ልጅ

“የሰብዓዊ ፍጡር ልጅ” ወይም “ከሰው የተወለደ ልጅ”። ሕዝቅኤል ሰው ብቻ መሆኑን አፅንዖት ለመስጠት እግዚአብሔር ሕዝቅኤልን እንዲህ በማለት ይጠራዋል። እግዚአብሔር ዘላለማዊና ኃያል ነው፣ ሰዎች ግን አይደሉም። ይህንን በሕዝቅኤል 2፡1 ላይ እንዴት እንደ ተረጎምከው ተመልከት። አ.ት፡ “ሟች ሰው” ወይም “ሰው”

ኩርንችትና እሾህ … ጊንጥ

እነዚህ ቃላት ሕዝቅኤል እግዚአብሔር የሚለውን በሚነግራቸው ጊዜ የእስራኤል ሕዝብ በቅንነት እንዳልተቀበሉት ይገልጻል። (ዘይቤአዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)

ኩርንችትና እሾህ

ኩርንችት ቅርንጫፉ የሚዋጋ ጫፍ ያለው ቁጥቋጦ ነው። በቅንርጫፉ ላይ ያሉት ሹሎች እሾህ ተብለው ይጠራሉ።

ጊንጥ

ጊንጥ ሁለት የፊት ለፊት ጥፍሮች፣ ስድስት እግሮችና አለብላቢ መናደፊያ ረጅም ጅራት ያለው ትንሽ እንስሳ ነው። ሲናደፍ በጣም ያሳምማል።

ቃላቸውን አትፍራ

“እነርሱ የሚናገሩትን አትፍራ”

ከፊታቸው የተነሣ አትደንግጥ

“ፊታቸው” የሚለው ቃል ሕዝቡ በፊት ገጽታቸው የሚያስተላልፉትን መልዕክት የሚያሳይ ፈሊጣዊ አነጋገር ነው። አ.ት፡ “አንተን ከሚያዩበት መንገድ የተነሣ እኔን ለማገልገል ያለህ ፍላጎት አይጥፋብህ” (ፈሊጣዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)