am_tn/ezk/02/04.md

1.7 KiB

ልጆቻቸው

በእግዚአብሔር ላይ አምፀው የነበሩትን የቀደመውን የእስራኤል ትውልድ ልጆች ሲሆን ሕዝቅኤል በሚጽፍበት ወቅት በእስራኤል የሚኖረውን ሕዝብ ያመለክታል።

የእልኸኝነት ፊት አላቸው

“እልኸኛ መሆናቸውን የሚያሳይ የፊት ገጽታ አላቸው”

እልኸኛ ፊትና ደንዳና ልብ

“እልኸኛ ፊት” የሚሉት ቃላት ውጫዊ እንቅስቃሴ የሚያደርጉበትን መንገድ የሚያመለክት ሲሆን “ደንዳና ልብ” የሚሉት ቃላት ደግሞ የሚያስቡበትንና የሚሰማቸውን መንገድ የሚያመለክቱ ናቸው። (See: Doublet)

እልኸኛ

ይህ የሚያስበውን ወይም የሚያደርገውን ለመቀየር እምቢተኛ የሚሆንን ሰው ይገልጻል።

ደንዳና ልብ

ዐለቶች መቼም ቢሆን እንደማይለወጡና እንደማይለሰልሱ ሁሉ እነዚህ ሰዎችም አይለወጡም፣ ክፉ ነገር በሚያደርጉበት ጊዜም አይጸጸቱም። (ዘይቤአዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)

ቤት

ይህ በቤቱ ውስጥ የሚኖሩትን ቤተሰቦች የሚያመለክት ፈሊጣዊ አነጋገር ነው፤ በመሆኑም፣ ይህ ከረጅም ዓመታት ጀምሮ ያሉትን የያዕቆብን ዘሮች፣ እስራኤላውያንን ያመለክታል። (ፈሊጣዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)

በመካከላቸው ነቢይ ነበረ

“ሊሰሙት ያልፈቀዱት ያ ሰው ነቢይ ነበር”