am_tn/ezk/02/01.md

1.5 KiB

ተናገረኝ

የአንተ ቋንቋ ተናጋሪውን መለየት ካለበት “አንድ ሰውን የሚመስል” በማለት ቢለየው ይመረጣል (ሕዝቅኤል 1፡26)። ያ “መንፈስ ቅዱስ” አልነበረም።

የሰው ልጅ

“የሰብዓዊ ፍጡር ልጅ” ወይም “ከሰው የተወለደ ልጅ”። ሕዝቅኤል ሰው ብቻ መሆኑን አፅንዖት ለመስጠት እግዚአብሔር ሕዝቅኤልን እንዲህ በማለት ይጠራዋል። እግዚአብሔር ዘላለማዊና ኃያል ነው፣ ሰዎች ግን አይደሉም። አ.ት፡ “ሟች ሰው” ወይም “ሰው”

መንፈስ ቅዱስ

ሊሆኑ የሚችሉ ሌሎች ትርጉሞች 1) “መንፈስ” ወይም 2) “ንፋስ” የሚሉት ናቸው።

ወደ እስራኤል ሕዝብ፣ በእኔ ላይ ወዳመፀው ወደ አመፀኛው ሕዝብ

“ወደ እስራኤላውያን፣ በእኔ ላይ ወዳመፁት አመፀኛ ሕዝቦች”። “የእስራኤል ሕዝብ” እና “አመፀኛ ሕዝብ” ሁለቱም ሐረጎች የሚያመለክቱት አንዱን ሕዝብ ነው። አ.ት፡ “ወደ እስራኤል ሕዝብ፣ በእኔ ላይ ወዳመፀው ሕዝብ” (See: Doublet)

እስከዚህ ቀን ድረስ

“አሁን እንኳን” ወይም “ዛሬም እንኳን”። ይህ ማለት የእስራኤል ሕዝብ እግዚአብሔርን ባለመታዘዝ ቀጥለዋል።