am_tn/ezk/01/27.md

2.7 KiB

ከወገቡ በላይ ያለው ገጽታ

ከወገቡ በላይ ያለው የሰውየው አካል እሳት ያለበት የጋለ ብረት ይመስል ነበር። የነገር ስም የሆነው “ገጽታ” እንደ ግሥ ሊተረጎም ይችላል። አ.ት፡ “ከወገቡ በላይ ይታይ የነበረው” (የነገር ስም የሚለውን ተመልከት)

ከወገቡ በታች ያለው ገጽታ ዙሪያው በሙሉ የእሳትና የብርሃን ገጽታ ነበረው

“ገጽታ” የሚለው የነገር ስም እንደ ግሥ ሊተረጎም ይችላል። አ.ት፡ “ወገቡ መስሎ ከሚታይ ገጽታው በታች ዙሪያው እሳትና ብሩህ ብርሃን የሚመስል አየሁ” (የነገር ስም የሚለውን ተመልከት)

በዝናባማ ቀን በደመና ውስጥ የሚታይ የቀስተ ደመና ገጽታን የሚመስል ብሩህ ብርሃን ከቦት ነበር

“ገጽታ” የሚለው የነገር ስም እንደ ግሥ ሊተረጎም ይችላል። አ.ት፡ “የከበበው ብሩህነት ልክ በዝናባማ ቀን በደመና ውስጥ የሚታየውን ቀስተ ደመና ይመስል ነበር” (የነገር ስም የሚለውን ተመልከት)

ቀስተ ደመና

ፀሐይ ከተመልካቹ በስተኋላ በምትወጣበት ጊዜ በዝናብ ውስጥ የሚታይ ልዩ ልዩ የብርሃን ቀለማት

እርሱም የእግዚአብሔር መልክ አምሳያ ነበር

“አምሳያ” የሚለው የነገር ስም ትርጉሙ ሕዝቅኤል ሲያየው የእግዚአብሔርን ክብር ይመስል የነበረው ነው። “አምሳያ” እና “መልክ” ሁለቱም ከግሣዊ ሐረግ ጋር ሊተረጎሙ ይችላሉ። አ.ት፡ “የእግዚአብሔርን ክብር መስሎ ይታይ ነበር” (የነገር ስም የሚለውን ተመልከት)

በግንባሬ ተደፋሁ

“በምድር ላይ ሰገድሁ” ወይም “በምድር ላይ ተጋደምሁ”። ሕዝቅኤል የወደቀው በአደጋ ምክንያት አይደለም። ወደ ምድር ዝቅ ያለው እግዚአብሔርን መፍራቱንና ማክበሩን ለማሳየት ነው። (የአነጋገር ዘይቤ የሚለውን ተመልከት)

አንድ የሚናገርን ድምፅ ሰማሁ

“ድምፅ” የሚለው ቃል ሰውን የሚወክል ፈሊጣዊ አነጋገር ነው። አ.ት፡ “አንድ ሰው ሲናገር ሰማሁ” ወይም “አንድ ሰው ተናገረ፣ እኔም ድምፁን ሰማሁ” (ፈሊጣዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)