am_tn/ezk/01/26.md

1.3 KiB

ከራሳቸው በላይ

“ከፍጡራኑ ራስ በላይ”

የዙፋን መልክ ነበረው

እዚህ ጋ፣ የነገር ስም የሆነው “መልክ” ማለት ሕዝቅኤል ዙፋን መስሎ የታየው ነበር። ቃሉ በግሣዊ ሐረግ ሊተረጎም ይችላል። አ.ት፡ “ዙፋን ይመስል ነበር” (የነገር ስም የሚለውን ተመልከት)

ሰንፔር

የጠራ ሰማያዊና በጣም አንጸባራቂ የሆነ በጣም ውድ ድንጋይ

የዙፋን መልክ በነበረው ላይ

የነገር ስም የሆነው “መልክ” በግሣዊ ሐረግ ሊተረጎም ይችላል። አ.ት፡ “ዙፋን በሚመስለው ላይ --- ነበር” (የነገር ስም የሚለውን ተመልከት)

መልኩ የሰው ገጽታ ያለው የሚመስል

የነገር ስሞች የሆኑት “መልክ” እና “ገጽታ” በግሣዊ ሐረጎች ሊተረጎሙ ይችላሉ። ይህ ማን እንደሆነ መናገር ከፈለግህ ምናልባት እግዚአብሔር እንደሆነ መናገር ይኖርብሃል (ሕዝቅኤል 1፡3)። አ.ት፡ “ሰውን መስሎ ከሚታየው ጋር የሚመሳስል አንዳች ነገር” (የነገር ስም የሚለውን ተመልከት)