am_tn/ezk/01/24.md

3.3 KiB

ከዚያም የክንፎቻቸውን ድምፅ ሰማሁ። እንደ ብዙ ውኆች ድምፅ ያለ፣ በሚሄዱበት ሁሉ እንደ ሁሉን ቻዩ ድምፅ ያለ።

“በሚሄዱበት ቦታ ሁሉ” የሚሉት ቃላት የሚያመለክቷቸው ሊሆኑ የሚችሉ ሌሎች ትርጉሞች 1) በዚህ ቁጥር ፊት ያሉት ቃላት ሁሉ “በሚሄዱበት ቦታ ሁሉ የክንፎቻቸውን ድምፅ ሰማሁ። እንደሚጎርፍ ውሃ ድምፅ ያለ፤ እንደ ሁሉን ቻዩ ድምፅ ያለ፤” ወይም 2) “ክንፎች፣ እንደሚጎርፍ ውሃ ድምፅ ያለ፤ እንደ ሁሉን ቻዩ ድምፅ ያለ፤ በሚሄዱበት ቦታ ሁሉ እንደ --- ያለ ድምፅ” የሚሉት ቃላት ይከተሏቸዋል የሚሉት ናቸው።

እንደ … ውኆች። እንደ … የሚሄዱበት። እንደ … የዝናብ ማዕበል። እንደ … ሰራዊት።

ሕዝቅኤል ባየው ነገር መደነቁን በማሳየት ላይ ስለ ነበር እነዚህ ዐረፍተ ነገሮች የተሟሉ አይደሉም። እንደ ሙሉ ዐረፍተ ነገር ሊተረጎሙ ይችላሉ፡ “ክንፎቹ እንደ … ውሃ ድምፅ ነበር። በሚሄዱበት እንደ … ድምፅ ነበር። እንደ … የዝናብ ማዕበል ድምፅ ነበር። እንደ … ሰራዊት ድምፅ ነበር” (See: Simile)

ብዙ ውኆች

ይህ ማለት በቀላሉ “ብዙ ውሃ” ማለት ነው። ይህ ከፍተኛ ድምፅ ያለውን ወንዝ ወይም ታላቅ ፏፏቴን ወይም በውቅያኖስ ላይ የሚጋጩ ሞገዶችን ሊያመለክት ይችላል። እነዚህ ሁሉ ከፍተኛ ድምፅ ያላቸው ናቸው።

እንደ ሁሉን ቻዩ ድምፅ ያለ

መጽሐፍ ቅዱስ አንዳንድ ጊዜ ነጎድጓድን እንደ “የሁሉን ቻዩ ድምፅ” አድርጎ ያመለክታል። አ.ት፡ “ድምፁ የሁሉን ቻዩን አምላክ ድምፅ ይመስል ነበር” ወይም “እርሱ የሁሉን ቻዩን ነጎድጓድ ድምፅ ይመስል ነበር” (ፈሊጣዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)

እንደ ዝናብ ማዕበል ድምፅ ያለ

ሊሆኑ የሚችሉ ትርጉሞች 1) “እንደ ታላቅ ማዕበል ድምፅ ያለ” ወይም 2) “እንደ ብዙ ሕዝብ ድምፅ ያለ” የሚሉት ናቸው። አ.ት፡ “እንደ ታላቅ ማዕበል ድምፅ ያለ ታላቅ ድምፅ ነበር” ወይም “እንደ ብዙ ሕዝብ ድምፅ ያለ ታላቅ ድምፅ ነበር” (See: Simile)

በሚቆሙበት ጊዜ ሁሉ

“ፍጡራኑ እንቅስቃሴያቸውን በሚያቆሙበት ጊዜ ሁሉ”

ክንፎቻቸውን ዝቅ ያደርጉ ነበር

“ፍጡራኑ ክንፎቻቸው በጎናቸው እንዲወርዱ ያደርጉ ነበር”። ይህንን ያደረጉት ክንፎቻቸውን ለመብረር በማይጠቀሙበት ጊዜ ነበር።

ከጠፈሩ በላይ አንድ ድምፅ መጣ

“ከጠፈሩ በላይ የነበረ አንድ ሰው ተናገረ”። ይህ የማን ድምፅ እንደሆነ መናገር ከፈለግህ ምናልባት የእግዚአብሔር ድምፅ እንደሆነ መግለጽ ይኖርብሃል (ሕዝቅኤል 1፡3)።