am_tn/ezk/01/22.md

1.5 KiB

የተስፋፋ የጠፈር መልክ

እዚህ ጋ፣ የነገር ስም የሆነው “መልክ” ማለት “የተስፋፋ የጠፈር መልክ” መስሎ ለሕዝቅኤል የታየው ነው። ቃሉ በግሣዊ ሐረግ ሊተረጎም ይችላል። አ.ት፡ “የተስፋፋ ጠፈር ይመስል የነበረው” (የነገር ስም የሚለውን ተመልከት)

የተስፋፋ ጠፈር

ጠፈሩ በግማሽ የተቆረጠ ክፍት ኳስ ይመስል ነበር። “የተስፋፋ” ማለት በጣም ሰፊ ማለት ነው። “ከላይ ወደ ታች የተደፋ ትልቅ ጓድጓዳ ሳህን”

ግርምት ቀስቃሽ መስታወት መሰል ድንጋይ

“ግርምት ቀስቃሽ በረዶ” ወይም “ሰዎች በሚያዩት ጊዜ እንዲደነቁ የሚያስደርጋቸው መስታወት መሰል ድንጋይ”

ከራሳቸው በላይ ተዘርግቷል

“ተስፋፊው ጠፈር ከፍጡራኑ ራስ በላይ ተዘርግቶ ነበር” ወይም “ተስፋፊው ጠፈር ከፍጡራኑ ራስ በላይ ሰፊ ቦታ ይዞ ነበር”

ከጠፈሩ ስር

“ከጠፈሩ በታች”

እያንዳንዱ ሕያዋን ፍጡራን ደግሞ ራሳቸውን የሚሸፍኑበት ጥንድ ክንፍ ነበራቸው፤ እያንዳንዱ የራሱን አካል የሚሸፍንበት ጥንድ ክንፍ ነበረው

“እያንዳንዱ ሕያው ፍጡር አካላቸውን የሚሸፍኑባቸው ሌላ ሁለት ክንፍ ነበራቸው”