am_tn/ezk/01/19.md

1.7 KiB

ሕያዋኑ ፍጡራን ከመሬት በሚነሡበት ጊዜ

ፍጡራኑ ምድርን ከለቀቁ በኋላ በአየር ላይ ይበሩ ነበር። አ.ት፡ “ፍጡራኑ ምድርን ለቀው ወደ አየር በሚወጡበት ጊዜ” (See: Assumed Knowledge and Implicit Information)

መንኩራኩሮቹም ደግሞ ወደ ላይ ተነሡ

“መንኩራኩሩም ደግሞ ምድርን ለቆ ወደ አየር ወጣ”

መንፈስ ወደሚሄድበት ሁሉ እነርሱም ሄዱ

“እነርሱ” የሚለው ቃል ፍጡራኑን ያመለክታል።

በአጠገባቸው መንኩራኩሮቹ ተነሡ

“መንኩራኩሮቹ ከሕያዋን ፍጡራኑ ጋር ወደ አየር ላይ ወጡ”

የሕያው ፍጡሩ መንፈስ በመንኩራኩሮቹ ውስጥ ነበር

ሊሆኑ የሚችሉ ትርጉሞች 1) ሕዝቅኤል አንድ ፍጡር የሆኑ በሚመስል መልኩ የሚናገረው በቁጥር 19 ስላሉት “ፍጡሮች” ነው። አ.ት፡ “የሕያዋን ፍጡራኑ መንፈስ በመንኩራኩሮቹ ውስጥ ነበር” ወይም 2) ሕዝቅኤል የአነጋገር ዘይቤን ይጠቀማል። አ.ት፡ “የሕይወት መንፈስ በመንኩራኩሮቹ ውስጥ ነበር” ወይም “ሕያው መንፈስ በመንኩራኩሮቹ ውስጥ ነበር” ወይም 3) በፍጡራኑና በመንኩራኩሮቹ ውስጥ የነበረው መንፈስ አንድ ነበር። አ.ት፡ “ለፍጡራኑ ሕይወት የሰጣቸው ያው መንፈስ ለመንኩራኩሮቹም ደግሞ ሕይወትን ሰጣቸው” የሚሉት ናቸው። (የአነጋገር ዘይቤ የሚለውን ተመልከት)